በጤናው ዘርፍ ከባለድርሻ ተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን ትኩረት በመስጠት እንደሚሰሩ የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ አስታወቁ።

    የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ላለፉት 10 ዓመታት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት እና በቀጣይ 10 ዓመታት ሊሰሩ የታቀዱ አንኳር ተግባራት ላይ በአስተዳደሩ ካሉ ባለድርሻ ተቋማት ጋር ውይይት አካሄዶል፡፡
    በወይይት መድረኩ የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ለምለም በዛብህ እንደተናገሩት ባለፉት 510 ዓመታት የእናቶችን ሞት መቀነስ፣ የህፃናትን ጤና ማሻሻያ፣ ተላላፊ የሆኑ በሽታዎችን መቆጣጠር፣ የጤና አገልግሎት ሽፋንን ማሳደግና ወባን መከላከል ላይ አበረታች ውጤቶችን ማስመዝገባቸውን በመግለፀ በአፈፃፀማቸው ዝቅተኛ የሆኑትን የቤተሰብ ምጣኔና የክትባት ሽፋን፣ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ክትትልና ህክምና ላይ በቀጣይ 10 አመት በልማት እቅዱ ትኩረት ሰተው እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡
    ኃላፊዋ ከዚህም ጋር አያይዘው በገጠር የጤና ተደራሽነትን የተሻለ ለማድረግ የጤና ተቋማትን በገጠርና በከተማ ቁጥር መጨመርና የመሰረተ ልማቶች አስፈፃሚ ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ በመስራትን ለቀጣይ 10 አመታት የተያዘውን እቅድ በተሻለ አፈፃፀም ለማከናወን መዘጋጀታቸውንም ገልፀዋል።
    የአስተዳደሩ ከንቲባው የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ አቶ መሀመድ ዑስማን ዘርፉ እየሰራቸው ላሉ ሥራዎች አስተዳደሩ የበኩሉን ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ገልፀው ከሌሎች ተቋማት ጋር ያለውን ቅንጅት በማሻሻል ዕቅዱን ሊያሳካ የሚችል ባለሞያ በአግባቡ የመጠቀም ችግር ባለፉት አመታት መኖሩን በመጠቆም የፋይናንስ ድጋፍን በማጠናከርና በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ አስተዳደሩ ትኩረት እንደሚሰጥና በተለይ የቀጣይ 10 ዓመታት ዕቅድ ለዘርፉ ከፍተኛ ለውጥን ሊያረጋግጥ የሚችል በመሆኑ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡
    የቀጣይ 10 ዓመታት መሪ ዕቅድ ያቀረቡት የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ የእቅድ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሪት ዳይሬክተር አቶ አለማየሁ ግርማ እንደገለፁት የዜጎችን ጤናና ደህንነት በማረጋገጥ፣ የጤና አገልግሎት ሽፋንን ማሳደግ፣ የጤናው ዘርፍ ትራንስፎርም ያደረገ ቤተሰብ መፍጠርን እና በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ እና በሁሉም ሀገር አቀፋ ፖሊሲዎች የጤናን ጉዳይ ማስረፅና የግል የጤናን ዘርፍ ተሳትፎ ማሳደግ ትኩረት የሚሰጥባቸው ጉዳዮች ናቸው ብለዋል፡፡
    በመድረኩ የተሳተፉ ባለድርሻ ተቋማት በሰጡት አስተያየትም ቅንጅታዊ አሰራሮች ማነስ፣ ለረጅም ጊዜ የዘርፉ ችግሮች የሆኑ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ጥናቶችን አለማካሄድና በጥናቶቹ ላይ የተመረኮዘ መፍትሄ አለማግኘት፣ የህክምና አገልግሎት ግብአቶች በየጊዜው መናርና የግል የጤና ተቋማትን ክትትል አለማድረግ የመሳሰሉት እንደ ሀገርም ሆነ እንደ አስተዳደር ትኩረት ተሰጥቶዋቸው መፈታት እንዳለባቸው የውይይቱ ተሳታፊዎች አንስተው በተለይም በቀጣይ ለታቀደው ዕቅድ መሳካት የበኩላቸውን ጥረት እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡