በትራፊክ አደጋ ይደርስ የነበር ሞትና የአካል ጉዳት ባለፉት ሶስት ወራት መቀነስ መቻሉን የትራፊክ ፖሊስ አስታወቀ::

    በአደጋ ሳቢያ ይደርስ የነበረ የንብረት ውድመትም እንዲሁ መቀነስ መቻሉን የትራፊክ ፖሊስ ጨምሮ ገልፆል::
    በድ/ዳ ፖለስ የትራፊክ ቁጥጥር ዳሪክቶሬት ዳሪክተር
    ኢ/ር ይሄነው ሽፈራሁ ከድሬ ፖሊስ ሚዲያ ጋር ከሩብ
    አመት አፈፃፀም ጋር ተያይዞ እባደረጉት ቆይታ እንደገለፁት ባለፈው 2013 የመጀመሪያ ሩብ አመት የ11 ሰዎች ህይወት በአደጋ ሲያልፍ በ41 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ገልፀው በዘንድሮ ሩብ በጀት
    አመት ግን የሞት ቁጥር በሶስት ቀንሶ ስምንት የሞት
    አደጋ ሲመዘገብ ከከባድ የአካል ጉዳትም ጋር ተያይዞ እንዲሁ በአንፃራዊነት በአስራ አንድ ቀንሶ ሰላሳ አንድ
    ብቻ መመዝገቡን ነው ያስታወቁት::
    ኢ/ር ይሄነው ሽፈራሁ ከደረሰ የንብረት ውድመት ጋር ተያይዞ እንደገለፁት በትራፊክ አደጋ ይደርስ ከነበረ የንብረት ውድመት አንፃርም እንዲሁ በ2013 የመጀመሪያ ሩብ አመት ከአምስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሺ ብር በላይ የንብረት ውድመት ሲመዘገብ በዘንድሮው ሩብ አመት ግን ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ የቀነሰ የንብረት ውድመት መመዝገቡን ነው የተናገሩት::
    ለእዚህ የተሻለ ውጤት መመዝገብ የትራፊክ ቁጥጥር ዳሪክቶሬት በጥናት ላይ በመመርኮዝ የሰራቸው የቁጥጥርና ተያያዥ ስራዎች በዋነኝነት ተጠቃሽ መሆናቸውን የተናገሩት ኢ/ር ይሄነው ሽፈራሁ ይህ ማለት ግን በቂ ነው ማለት አይደለም በቀጣይም በትራፊክ አደጋ የአንድም ሰው ህይወት እንዳያልፍ እዚህም በተሻለ መልኩ የሚሰራ ይሆናል ብለዋል::
    ሃላፊው በቆይታቸው መጨረሻ ባስተለፉት መልዕክት የትራፊክ አደጋን መከላከል የትራፊክ ፖሊስ ብቻ ሳይሆን የሁሉንም አካላትና የህ/ብ እገዛና ትብብር የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል::