የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዐል በሠላም ይከበር ዘንድ
የሁላችንም ሀላፊነት ነው
እንኳን ለ16ኛው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዐል በሠላም አደረሳችሁ፡፡ ዘንድሮ የሚከበረው የብሄር-ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዐል ከሌላው ግዜ ለየት የሚያደርገው አገራችን ኢትዮጱያ አንድነቷን በማይፈልጉ ስግብግቡ የህወሀታ ጁንታ አሸባሪ ቡድን፣ ጀሌዎቹ እና የውጪ ታሪካዊ ጠላቶቻችን እናት አገራችንን ለማፍረስ ተነስተው ለህልውናዋ እና ሉዓላዊነቷ መከበር ዘመቻ ላይ ባለንብት ወቅት፤ እንዲሁም አዲስ መንግስት ከተመሰረተ በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ በአስተዳደራችን በልዩ ሁኔታ መከበሩ ነው፡፡
አገራችን ኢትዮጵያ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች እና የተለያዩ የእምነት ተከታዮች በአንድነት በመከባበር፣ በመፈቃቀር እና በመተሳሰብ የሚኖርባት ለዓለም ምሳሌ የሆነች አገር ናት፡፡ እንደ አስተዳደራችን የበረሀዋ ንግስት ድሬዳዋ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦችና የተለያዩ የእምነት ተከታዮች በፍቅር፣ በመቻቻል፣ በመከባበር፣ በአንድነት፣ በመተሳሰብ እና በመደጋገፍ የሚኖሩባት ለሌሎች ዓለማት ሁሉ ማሳያ ከተማ ነች፡፡ ይኸው የብሄር ብሄረሰቦች እና የተለያዩ እምነት ተከታዮች አብሮ የመኖር ባህላችን የሀገራችን ብሎም የከተማችን መገለጫ በሆነ ወቅት የሚቆም ሳይሆን ለሁል ጊዜው አጠንክረን ልንጨብጠው እንደ ሚገባ እሙን ነው፡፡ ስለሆነም በተለመደ መልኩ የበረሀዋ ንግስት ድሬደዋ የምትታወቅበት የሰላም፣ የፍቅር እና እንግዳ ተቀባይነት ባህላችን በዓሉን ሁላችንም በሰላም እንድናከበረው ትልቅ አስተዋፅኦ አለው፡፡
የዘንድሮ ብሄር ብሄረሰቦች ቀን ለአስተዳደራችን ትልቅ አስተዋፅኦ አለው፡፡ ይህ ለአስተዳደራችን ከለውጥ ማግስት የተገኘ እድል ለከተማች አሁን ያለው አዲስ የተመሰረተው መንግስት እያሳየ ያለውን ለውጥ የበለጠ እንዲሰራና የከተማችን እድገት ያለበት ሁኔታ ታይቶ ያሉብንን ችግሮች የሚፈታበት ምዕራፍነው፡፡
ነገር ግን ይህ እንዲሳካ የማይፈልጉ የከሃዲ፣ ጁንታው አሸባሪ ቡድን ተላላኪ ሰርጎገቦች ተመሳስለውና ራሳቸውን ለውጠው፤ ሠላማዊ ሰው በመምሰል የበዐሉን ሠላም እንዳያውኩ ጥንቃቄ መደረግ አለበት፡፡ ለዚህ ደግሞ ትልቁ ኃላፊነት ያለው በመላው የድሬደዋ ሠላም ወዳድ ነዋሪ ላይ ነው፡፡ ስለሆነም ይህን ኃላፊነት ለመወጣት ከመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ጋር በመደማመጥ እና በመተባበር በአካባቢያችን ጸጉረ-ልውጥ እና እንግዳ ነገር ስንመለከት ቀድሞ በማሳወቅ ተልዕኳቸውን ልናከሽፍ ይገባል፡፡ በአንድነት ከቆምን ከእኛ ምንም ሊያመልጥ የሚችል ከሀዲና አስመሳይ ቡድን ሊኖር ስለማይችል ለበዐሉ በሠላም መከበር በጽናት እንቁም፡፡
በሌላ በኩል ሳንዘናጋ ለኮሮና ቫይረስ ጥንቃቄ መርሆዎች ማስክ በማድረግ፣ እጅን በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ ወይም ሳኒታይዘር በመጠቀም፣ ርቀታችንን በሁለት ሜትር በመጠበቅ ራሳችንን፣ ቤተሰቦቻችንን እና ማህበረሰባችንን ብሎም መላውወገኖቻችንን ከኮሮናቫይረስ/ ከኮቪድ19 ልንከላከል እንዲሁም ኃላፊነታችንንም በመወጣት በዓሉ ያለምንም ችግር ይከበር ዘንድ የሁላችንም ሚና ላቅ ያለ መሆኑን በተግባር ልናሳይ ይገባል፡፡
የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዐል ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ ደምቃና በገናናነቷ የአፍሪካውያን ኩራትና የብልፅግና ተምሳሌት ሆኖ የምትታይበት የጀግኖች ልጆቻ ታሪክ በወርቅ መዝገብ የሚፃፍበት ዘመን እንዲሆን እየተመኝን ለእኛ ድሬዳዋዊያን ወንድማማችነታችን የበለጠ ተጠናክሮ ፍቅርና አብሮነት ለአለም ህዝብ ተምሳሌትነታችን ሚቀጥልበት ዘመን ይሆናል፡፡ እንኳን ለ16ኛው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዐል በሰላም አደረሳችሁ፡፡
ወንድማማችነት ለህብረብሔራዊ አንድነት
መንግስትኮሙኒኬሽንጉዳዮችቢሮ
ድሬዳዋ
24/3/2014 ዓ/ም


