ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አፍሪካ በፀጥታው ም/ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት እንደሚታገሉ አሳወቁ::

    ኅዳር 29/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት ከሌሎች የአፍሪካ አገራት መሪዎች ጋር እንደሚታገሉ አሳወቁ፡፡
    1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ሕዝብ ያላት አኅጉሪቱ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ ሊኖራት እንደሚገባ ነው በቲውተር ገጻቸው የጻፉት፡፡
    በአኅጉሪቱ ጉዳዮች ላይ የሚደረግ ምክክር ያለአኅጉሪቱ ተወካይ እየተካሄደ የሚቀጥልበት አግባብ መቆም እንዳለበትም አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡