የበዓሉ አከባበር ሂደት ተገመገመ:-
በግምገማው :-
** ከጸጥታ አንጻር ከአጎራባች ክልሎች ጋር በመሰራቱ በዓሉ በሰላምና ካለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ማስቻሉ::
** እንግዶችን በየደረጃው ከማስተናገድ አንጻር በተሳካ ሁኔታ መፈጸሙ።
** ለነዋሪውና ለእንግዶች ተጠቃሚ ያደረገ የሀገር ውስጥ አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርትና አገልግሎታቸውን ለማስተዋወቅ እንደዚሁም ለገበያ ለማቅረብ ያስቻለ ከሀገር ውስጥ ባለፈ የአጎራባች ሀገሮች አምራቾችን ያካተተ የንግድ ትርኢትና ባዛር በተሳካ ሁኔታ መከናወኑን::
** ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊት የሚውል ደም ለወገኔ በሚል መሪ ቃል ደም የመለገስ ስነስርአት መከናወኑን::
** የዜጎች ወንድማማችነትን ከማጎልበት የብሔር ብሔረሰቦች የበለጠ እንዲተዋወቁ እና እንዲተሳሰሩ ሚያስችሉ ስነስርዓቶች መከናወናቸው::
በአጠቃላይ በዓሉ ድሬዳዋን መልካም ገጽታ ገንብቶ ያለፈ እንደሆነ ለመገምገም ተችሏል፡፡


