የበዓሉን አከባበር አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የአስተዳደሩ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ እስቅያስ ታፈሰ እንደገለፁት
የ16ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ሦስት መሰረታዊ አላማዋች ይዞ የቅድመ ዝግጅት ስራው ሲከናወን መቆየቱን ገልፀዋል።
እንደ ኃላፊው ገለፃ
_የከተማዋን ሰላማዊነትና የቀደመ ማንነቷን ጠብቃ የቀጠለች መሆኗን፣እሴቶቻችን በነበሩበት የቀጠሉ እና ቀደም ሲል በተለያየ መልኩ ሲገለጽ የነበረው ገፀታን የማጠልሸትና እሴቶቻችን የተሸረሸሩበት ሁኔታ ሲነሱ የነበሩበትን ነባራዊ ሁኔታ የቀየረ እንዲሆንና የአብሮነት የፍቅርና የአንድነት የመቻቻል ከተማ መሆኗን በተጨባጭ ለማሳየት።
_በአሉን በመልካም አጋጣሚነት በመጠቀም አመራሩ የጀመራቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዋችን ስኬታማ ለማድረግና ከፌደራሊዚም ስርአቱ ጋር ተያይዞ የመጡትን መልካም ነገሮች አንዳለ በመውሰድ ቀደም ሲል ባሉ አመታት ከፌደራሊዚሙ ጋር ተያይዞ የነበሩብንን ተግዳሮቶች በሲንፖዚዩሙ በማሳየት ታዳሚው ስለድሬደዋ በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው ከማድረግ ባለፈ ውሳኔ ሰጪና የህግ አካላት በመታደማቸው የቤት ስራ የሚሰጥ የፖናል ውይይት ሰነድ በማዘጋጀትም የህዝብ ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ መደረጉ።
_በአሉ በፍፁም ሰላማዊና ድሬዳዊ ጨዋነት ምንም አይነት የፀጥታ ኮሽታ ሳይኖር መጠናቀቁንና የመጡ እንግዶች ድሬደዋን ከሚያውቃት በላይ የተረዱበትና እውነትን ያረጋገጡበትና ሰላማዊ እንዲሁም የነበሩ እሴቶቿ የቀጠሉበት ሁኔታ የተረዱበት በአል ሆኖ መጠናቀቁ ስኬታማ ነበር ብለዋል።
እንደ ኃላፊው ገለፃ ድሬዳዋ ገፅታ ለመገንባት ያሏትን ቅርሶች፣ታሪኮችና ባህሎች እንዲሁም የልማት እድሉች ያሏት መሆኖን ለማሳየት የአገር አቀፍ የሚዲያ ጉብኝት በማድረግ የአስተዳደሩን የቱሪስት መስህብነትና የስልጣኔ መነሻና አሁንም የተሻለ እድል እንዳላት የሚያሳይ እድሎች እንዷሏት ስራዎች ተሰርቷል።
ካለው ሀገራዊ ወቅታዊ ሁኔታ የፀጥታው ሁኔታ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ የአስተዳደሩ ነዋሪዋች የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን የፀጥታ አካላት አቀናጅቶ መስራቱ እንዲሁም የፀጥታ ተባባሪና በጎ ፍቃድ ወጣቶች ከፖሊስ ጋር በመቀናጀት በአሉ በአስተማማኝ ፀጥታ እንዲያልፍ አስተዋፅዖ በማበርከታቸው አስተዳደሩ ምስጋና ያቀርባል ብለዋል።
ድሬደዋ ሞተር የለገሀር አደባባይ ኮንሰርት ሙሉ ወጪ በመቻል በአሉ ድምቀት እንዲኖረው ማረህብረሰቡን እንዲነሳሳ በማድረጉ እንዲሁም ሌሎች አካላት ለበዓሉ ድምቀት አስተዋፅዖ ላበረከቱ ሁሉ በአስተዳደሩ ስም ምስጋና አቅርበዋል።
በመጨረሻም ኃላፊው ለአስተዳደሩ ነዋሪዋች ባስተላለፉት መልዕክት በከተማዋ የልማትና የለውጥ ስራዋች በአዲስ ምዕራፍ ወደ ስራ በገባበት መሰረት አስተዳደሩ የተጀመሩ ልማቶችና እንቅስቃሴዋች ለህብረተሰቡ በገባነው ቃል መሰረት እንደሚሰራ ገልፀዋል።


