በዋሂል ክላስተር ነዋሪውን ተጠቃሚ የሚያደጉ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ መሆኑ ተገለፀ

    የፕሮጀክቶቹ አፈፃፀም ያለበት ደረጃ ጉብኝት ተደርጓል
    በክላስተሩ በከፍተኛ ወጪ እየተገነቡ ያሉ የመስኖ ልማት እንደዚሁም የችግኝ ጣቢያ ልማትስራዎች የተጎበኙ ሲሆን በቀጣይ በአፋጣኝ ወደስራ ለማስገባት በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ ከማህበረሰቡ ጋር ውይይት ተደርጓል ።
    የድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ሱልጣን አልዪ አየተገነቡ ያሉት የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች በአካባቢው ያለውን የነዋሪውን ጥያቄ ምላሽ በመስጠት የአራሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ከፍ ማድረግ የሚያስችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል ።
    ፕሮጀክቶቹ አርሶአደሩን በአመት ከአንድ ጊዜ በላይ እንዲያመርት በማስቻል እንዲሁም ከቋሚ ሰብል ባለፈ ለፍጆታ የሚውሉ ምርቶችን በማምረት በምግብ እራስን ለመቻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አቶ ሱልጣን አልዪ ጨምረው ገልጸዋል።
    ከአፈፃፀም አኳያ ያሉ እክሎችን ለመቅረፍ ቁርጠኛ የአመራር ውሳኔ ከማሳለፍ ባለፈ ህብረተሰቡ ለፕሮጀክቶቹ መጠናቀቅ እና ወደስራ እንዲገቡ ከማስቻል አንፃር ሊያበረክቱ የሚገባቸውን ድጋፍ በተመለከተ ውይይት ተደርጎ መግባባት ላይ መደረሱን የቢሮ ሃላፊው አስረድተዋል።
    የድሬዳዋ አስተዳደር የደንና አየርንብረት ለውጥ ባለስልጣን የደን ልማትና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ማስረሻ ይመር በክላስተሩ በፕሮጀክት ደረጃ ሲመሩ የነበሩ የችግኝ ጣቢያዎች የፕሮጀክት ጊዜያቸው ሲያበቃ በህብረተሰቡ ባለቤትነት እንዲመሩ ለማስቻል ስራ እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል።