በአስተዳደሩ ካሉት የመንግስት ጤና ተቋማት በሙሉ የማህፀን በር ካንሰር የነፃ ምርመራ አገልግሎት እየተሰጠ እንደሚገኘ ተጠቆመ።
በሀገራችን ሴቶችን ለከፋ ችግር እያጋለጡ ከሚገኙ በሽታዎች አንዱና በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ ያለውን የካንሰር ዓይነቶች መካከል የማህፀን በር ካንሰር ነው። የካንሰር ህመም በሰውነታችን ውስጥ መከሰት የሚጀምረው ሴሎች ከቁጥጥር ውጪ በሆነ ሁኔታ ማደግ በሚጀምሩበት ወቅት ነው። በዚህም ከቁጥጥር ውጪ በሆነ ህደት አን የነበረው ሴል ከሁለት በላይ በመራባት ብዛት ያላቸው የካንሰር ሴሎችን ወይም ቲዩመር በመፍጠር የካንሰር ህመም መከሰት…


