በአስተዳደሩ ካሉት የመንግስት ጤና ተቋማት በሙሉ የማህፀን በር ካንሰር የነፃ ምርመራ አገልግሎት እየተሰጠ እንደሚገኘ ተጠቆመ።

    በሀገራችን ሴቶችን ለከፋ ችግር እያጋለጡ ከሚገኙ በሽታዎች አንዱና በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ ያለውን የካንሰር ዓይነቶች መካከል የማህፀን በር ካንሰር ነው። የካንሰር ህመም በሰውነታችን ውስጥ መከሰት የሚጀምረው ሴሎች ከቁጥጥር ውጪ በሆነ ሁኔታ ማደግ በሚጀምሩበት ወቅት ነው።
    በዚህም ከቁጥጥር ውጪ በሆነ ህደት አን የነበረው ሴል ከሁለት በላይ በመራባት ብዛት ያላቸው የካንሰር ሴሎችን ወይም ቲዩመር በመፍጠር የካንሰር ህመም መከሰት ይጀምራል።
    ይህንን በሴቶች ላይ የሚከሰተው የማህፀን በር ካንሰር በአስተዳደራች ያሉት የመንግስት ጤና ተቋማት ውስጥ እድሜያቸው ከ15 እስከ 49 አመት የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሴቶችን የነፃ ቅድመ ምርመራና የህክምና አገልግሎት መሰጠት ላይ እንደሚገኝ የድሬዳዋ ዩኒቨሪሲቲ የማህፀን ስፕሻሊስት የሆኑት ዶ/ር ታፈሰ ዳጀኔ ተናግረዋል።
    አክሎም ዶ/ር ታፈሰ ለሚዲያ ባለሞያ በችግሩ ሱሪያ ላይ እና የሚዲያ ድርሻ ምን መሆን እንዳለበት የሚያጠነጥን የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ላይ ካንሰር ዓይነት ሂውማን ፓፒሎን ቫይረስ በተሰኘ ረቂቅ ተህዋሰሰ አማካኝነት የሚከሰት በመሆኑ ተህዋስያኑ የማህፀን በር ህዋሳትን በመውረር ጤናማ ያልሆነ እድገትና ብዜትን እያስከተለ ወደ ሌሎች የአካል ክፍሎች በመሰራጨት የሰውነታችን ተለምዶኣዊ ተግባር በማወክ የብዙ ሴቶችን ህይወት በመንጠቅ የሀገራችን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን እያስከተለ ይገኛል ብለዋል።
    ይሁን እንጂ በሽታው ስር ሳይሰድ በቀላል ምርመራና ህክምና ታክሞ መዳን ስለሚቻል ከ30-49አመት የሆናቸው ሴቶች ወቅታዊና ተከታታይ ምርመራ በማድረግ በሽታው ተባብሶ ለህይወት አስጊ ከመሆኑ በፊት ማከም ይቻላል።