በድሬዳዋ አስተዳደር አዲስ መንግስት ከመመስረቱ ጋር ተያይዞ የድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ዘርፈ-ቡዙ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል ። ከዚህ ጋር ተያይዞ የመንግስት አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት በተለይም በተገልጋይ ላይ የሚያደርሱትን ጫና ለመቀነስ ፣ የአገልጋይነት መንፈስን የተላበሰ የስነ-ምግባር ችግር የሚስተዋልበትና ለዜጎች አፋጣኝ የሆነ ምላሽ የማይሰጥና ተጠያቂነት ባልሰፈነበት ሁኔታ የደበዘዘውን የሲቪል ሰርቫንትን ገፅታ ለመቀየርና ለማስተካከል ይቻል ዘንድ የተለያዩ ስልጠናዎችን በመውሰድና ከፌደራል መንግስት የተገኙ ተሞክሮዎችን መውሰድ ተችሏል።
ይህንንም ተሞክሮ መሰረት በማድረግ በተለይም በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ለነዋሪው ህብረተሰብ የሚሰጡትን አገልግሎት ጤናማ ለማድረግና ተገቢውን መልስ መስጠት የሚችል ብሎም በስነ-ምግባር የተመሰገነ ሰራተኛን ለመፍጠር ይቻል ዘንድ እቅድ በማውጣትና ከተቋም በመጀመር ተቋሙም የለውጥ ስራዎች የሚያስተገብር ቡድን እንዲፈጥር በማድረግ ሁሉም ተቋማት ተደራሽ እንዲሆኑ የተለያዩ ስራዎች መሰራታቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ አቡበከር አዶሽ ተናግረዋል ።
አቶ አቡበከር አክለውም ከለውጥ ስራዎች ጋር ተያይዞ ከዚህ በፊት ችግሮች እንደነበሩና አሁን ላይ ግን ለስራ የሚመች አሰራር መዘርጋት አስፈላጊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ዘርፈ-ቡዙ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረው ከመልካም አስተዳደር ስራዎች ጋር ተያይዞም ሁሉም ተቋማት እቅድ አውጥተው የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የሚፈቱበት ሁኔታ የመፍጠር ስራ መሰራቱንም ነው አቶ አቡበከር አዶሽ የተናገሩት ።
ሁሉም ተቋማት የመልካም አስተዳደርና የሪብራንዲንግ እቅድ ላይ ከተወያዩ በኋላ ሰራተኞች ከአመራሩና ከማኔጅመንቱ ጋር የጋራ በማድረግ ወደ ስራ እንደገቡ አቶ አቡበከር ተናግረው በተለይም በያዝነው አመት ለአስተዳደሩ ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥና ደረጃ ለማውጣት መታቀዱንና ይህም ተቋማት የተቀመጡትን መስፈርቶች አሟልተው እየሰሩ እንደሚገኝ በመገምገም በክቡር ምክትል ከንቲባው በሚመራው የመንግስት ተቋማትና የልማት ስራዎች ኮሚቴ ተቋቁሞ ለሲቪል ሰርቪስ ከተሰጠው ተልእኮ ጋር ተያይዞ በአስተዳደሩ ካሉና በብዛት የህዝብ አገልግሎት ጥያቄ ያለባቸው አምስት ተቋማት ተለይተው ሁሉም ተቋማትን ተደራሽ የሚያደርግ ስራ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ወደ ስራ መግባታቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ አቡበከር አዶሽ ገልፀዋል ።
በተለይም አሁን ላይ እየተሰሩ ካሉት ስራዎች የሚጠበቀው እያንዳንዱ ተቋም የመንግስት አገልግሎት ለመስጠት እቅድ መኖሩንና እቅዱንም ወደ ሰራተኛው ማውረዱን ፣ ሰራተኛውና ማኔጅመንቱ የግንኙነት አግባባቸው ጤናማ መሆኑን እንደሚታይና የመንግስት ስራ ህዝብን ማርካት የሚያስችል ቁመና ላይ ማምጣት የሚቻለውም የተቀናጀ የመንግስት አሰራር መስጠት ሲቻል መሆኑን አቶ አቡበከር ተናግረዋል ።
የድሬዳዋ አስተዳደር ነዋሪዎች የሚጠይቁት የአገልግሎት ፍላጎት ከመስፋት ጋር ተያይዞ እንደ አስተዳደር ከፍተኛ አስተዳደሩ ቁርጠኝነት በመውሰድ የድሬዳዋ የአደረጃጀት ጥናት ተሰርቶ ለምክር ቤት እንደሚቀርብና ይህም አደረጃጀት መመለስ የሚችላቸው ቡዙ ነገሮች እንደሚኖሩም አቶ አቡበከር ተናግረው የድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ከተሰጠው ተልእኮዎች አንዱ የመንግስት አገልግሎትን ዘመኑ የሚጠይቀውን መሳሪያ በመጠቀም የመንግስት ሰራተኞች ተገቢውን አገልግሎት መስጠት የሚችሉበት ሁኔታ እንዲመጡ ማድረግ መሆኑንም የድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ አቡበከር አዶሽ ተናግረዋል ።
ይህ በእንዲህ እንዳለም አሸባሪው ህወሀትና ተላላኪዎቹ በሀገራችን ኢትዮጲያ ላይ ከከፈቱት ግልፅ ጦርነት ጋር ተያይዞ ቤት ንብረታቸውን ጥለው ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን ይሆን ዘንድ ለወገን ደራሽ ወገን ነው በማለት የድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሰራተኞች የተሰበሰቡ አልባሳትን ለድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ድጋፍን አስረክበዋል ።


