የህብረተሰብ ተሳትፎ ልማት ኤጀንሲ ከUIIDP UNIT ጋር በመተባበር ለቀበሌ አመራሮችና አብይ የልማት ኮሜወቴዎች እንዲሁም ለህብረተሰብ ልማት ባለሙያዎች ከህብረተሰቡ እና ከሌሎች ለጋሽ ድርጅቶች የሚሰበሰብን ሀብት ማስተዳደር፣ አጠቃቀምና በፉይናስ አሰራር ዙሪያ በተዘጋጀ መመሪያ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መሰጠት ተጀመረ።
በዛሬው እለት በተዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የአስተዳደሩ የብልፅግና ፖርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሻክር አህመድ እንደተናገሩት የህብረተሰብ ተሳትፎ የልማት ኘሮጀክቶች ከህብረተሰቡ የተነሱ የልማት ስራ ችግር ይፈታሉ ተብሉ የተያዙ ኘሮጀክቶች የምናከናውንበት በመሆኑ ሁላችንም ጥያቄያቸውን ለመመለስ ሀላፊነታችንን መወጣት አለብን ብለዋል።
የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሻክር ከዚህም ጋር አያይዘው ከማህበረሰብ የምንሰበስባቸው ሀብቶችን በአግባቡ በመጠቀም ዘርፈ ብዙ የልማት ኘሮጀክቶች ስራዎችን መስራት እንችላለን በማለት ይህ ሳይሆን ከቀረ እራሱን የቻለ አሉታዊ ተፅእኖ ያመጣል ብለዋል።
የድሬዳዋ ህብረተሰብ ተሳትፎ እና ልማት ኤጀንሲ ስራ አሰኪያጅ ወ/ሮ ረሂማ አወል በበኩላቸው እንደተናገሩት ኤጀንሲው በአዋጅ ከተቋቋመበት አላማ አኳያ ህብረተሰቡን በማሳተፍ የተገኘውን የገንዘብ፣ የእውቀትና የክህሎት ሀብት በማሰባሰብ ህብረተሰቡ የሚፈልጋቸውን የልማት ጥያቄዋች ለመመለስ 40 % ከህዝቡ 60% ከመንግስት በማድረግ ከህብረተሰቡ የተነሱ የልማት ጥያቄዎች ይሰራሉ ብለዋል።
ኤጀንሲ ስራ አሰኪያጅ ወ/ሮ ረሂማ አክለውም ቀደም ሲል የሚሰሩ የልማት ኘሮጀክቶች ለጥራት ችግራቸው ዋና እና አንደኛው ምክንያት የገቢ አሰባሰቡ ለምዝበራ የተጋለጠ በመሆኑ የፋይናንስ አቅሙ ለተፈለገው የልማት ኘሮጀክት ውጭም እየዋሉ ያሉበት ሁኔታ መኖሩን ከ2009 እስከ 2013 ዓ.ም ያለው የኦዲት ግኝት ያሳያል ይህም በመሆኑ ከአሰራር ውጭ የሆነውን አሰራሮች ለማስቀረት አዲስ መመሪያ በማዘገጀት ባለድርሻ አካላት ግንዛቤ ወስደው መመሪያውን ተግባራዊ በማድረግ ድሬዳዋን ማስዋብ የሚችል ኘሮጀክቶች ማከናወን እንዲቻል መድረኩ መዘጋጀቱን ገልፀዋል።


