የፅዳት ዘመቻው ማህበረስቡ አካባቢውን በራሱ ተነሳሽነት አካባቢውን እንዲያፀዳና ህዝባዊ ሆኖ እንዲቀጥል እንደሚደረግ የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ሃርቢ ቡህ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ፓርኩን በአዲስ ዲዛይን ተሰርቶ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እድሳት በማድረግ ለድሬደዋ ልዩ ገፅታ የሚያላብስ ለማድረግ ዝግጅቶች እየተጠናቀቀ መሆኑን የድሬደዋ አስተዳደር ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ሱልጣን አሊዪ ገልፀዋል።አቶ ሱልጣን አያይዘውም ፕሮጀክቶችን በሚፈለገውሸጊዜና ትራት ከመፈፀም አኳያ ሁሉም አመራር በቁርጠኝነት እንዲንቀሳቀስ ጥሪ አቅርበዋል።


