የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሐር የቁልቢ ገብርኤል አመታዊ የንግስ ክብረ በዓል በተመለከተ ያስተላለፉት መልዕክት

    ድሬዳዋችን በዓመት 2 ጊዜ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች፤ አመታዊውን የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓል ለማክበር በሚመጡ እንግዶች ትደምቃለች። ዘንድሮም አስተዳደራችን በአሉን ለማክበር የሚመጡ እንግዶችን በፍቅር ተቀብሎ ለመሸኘት፤ መላው የፀጥታ ሀይሎች ደግሞ በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ለማስቻል ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል።
    ይህ በዓል ከኃይማኖታዊ ስርዓቱ ውጪ፤ ለአስተዳደራችን የሚያበረክተው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እጅግ ከፍተኛ ነው። ስለዚህ በአስተዳደራችን የምትገኙ ነጋዴዎች፣ የምግብ፣ የመጠጥና፣ የመኝታ እንዲሁም የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች በሙሉ፤ አግባብ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ከማድረግ እንድትቆጠቡ እያሳሰብኩ፤ ድሬዳዋችን ሁልጊዜም የእንግዶች ቀዳሚ ምርጫቸው እንድትሆን፤ ዘወትር በምንታወቅበት የእንግዳ ተቀባይነት አኩሪ ባህላችን አገልግሎት እንድትሰጡና፤ የድሬዳዋ አምባሳደርነት ሚናችሁን እንድትወጡ ጥሪ አቀርባለሁ።
    ታህሳስ 15/2014 ዓ.ም