የድሬዳዋ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ፖሪዘዳንት ነጂብ ኢድሪስ በስልጠና ላይ ባስተላለፉት መልእክት እንደተናገሩት ፍርድ ቤቶቹ ከዚህ ቀደም በህግ ከተሰጣቸው ስልጣን አንጻር ዳኞቹ ሲያዩዋቸው የነበሩት ጉዳዮችና ህጎች ውስን የነበሩ በመሆኑ ብቃት ያላቸው ዳኞችን ለማፍራት እንዲቻል ለፍርድ ቤቶቹ ዳኞች የአስተዳደር ሰራተኞች እና ለድጋፍ ሰጪ ባለሞያዎች ተከታታይነት ያለው ስልጠና መስጠት አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ፖሪዘዳንት ነጂብ ኢድሪስ ከዚህም ጋር አያይዘው መሰረታዊ ህጉንና የስነ- ስርአት ህጉን የተከተለ ህጋዊ የክርክር ሂደት እና ጥራት ያለው ውሳኔ ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ለመስጠት እንዲያስችል ታስቦ መድረኩ መዘጋጀቱን ገልፀዋል።
እንደ ፖሪዘዳንት ነጂብ ገለፃ ለፍርድ ቤት የሚቀርቡ ጉዳዮች ላይ ፈጣን ፤ ቀልጣፋ ፤ ጥራት ያለው እና ተአማኒ የሆነ ፍትህ በመስጠት ረገድ በዘርፉ ሁሉም የፍትህ ተቋማት ቅንጅታዊ አሰራራቸውና ሊያጠናክሩ ይገባል ብለዋል፡፡
የግንዛቤ ማዳበሪያ ስልጠና ለ4 ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ ከመድረክ ተገልፆል።


