ለአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር አስፋላጊ የሆኑ የቅድመ-ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ ተገለፀ

በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ {ዶ/ር}የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር በተለይም ባለፍት አመታት በሀገራችን ብሎም በድሬዳዋ አስተዳደር በርካታ ችግኞችን መትከል ተችሏል ። በድሬዳዋ አስተዳደርም በያዝነው አመት በከተማም ሆነ በገጠር ከ 3 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ችግኞች የሚተከሉ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞም ለሚተከተሉት ችግኞች የሚሆኑ የጉድጓድ ቁፋሮ በዛሬው እለት ተካሄዶል ።

በያዝነው አመት እንደ አስተዳደር ከ 3 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ለመትከል መታቀዱን የድሬዳዋ አስተዳደር ፅዳት እና ውበት ኤጀንሲ ሀላፊ አቶ አብዱረህማን መሀመድ ተናግረው በአስተዳደሩ ከሚተከሉት 3 ሚሊዮን ችግኞች ውስጥ በከተማ 1 ሚሊዮን ችግኞች እንደሚተከሉና ለዚህም የሚሆን የጉድጓድ ቁፋሮዎች እየተደረገ እንደሚገኝም ነው አቶ አብዱረህማን ያስታወቁት

በአስተዳደር ደረጃ ለሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር የጉድጓድ ቁፏሮዎች መደረጋቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር ፅዳት እና ውበት የውበት እና አረንጓዴ ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሸምሱዲን አሚን ተናግረው በቀጣይም በተቆፈሩት ጉድጓዶቹ ውስጥ ችግኞችን ከመትከል ባለፈ ችግኞቹን ተንከባክቦ የማፅደቅ ስራ እንደሚሰራም ነው አቶ ሸምሱዲን የተናገሩት ።

የአስተዳደሩ ነዋሪዎች እንዲሁም በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች በአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላዎች ላይ እንዲሳተፍ በርካታ ስራዎች እየተሰራ እንደሚገኝም ነው ድሬዳዋ አስተዳደር የፍትህና ፀጥታ ህግ ጉዳዮች ቢሮ የሰላም ሚኒስቴር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ኡሶ ሀሰን እንዲሁም የ 04 ወረዳ ስራ አስኪያጅ አቶ ያሲን ኡስማኤል ያስታወቁት ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *