የጅቡቲ ከተማ ከንቲባ አቶ ሰኢድ ዳውድ በትላንትናው እለት በድሬዳዋ አሰተዳደር በተለምዶ አሸዋ ተብሎ የሚጠራው ገበያ ቦታ የደረሰውን የእሳት አደጋ ማዘናቸው ገለፁ፡፡

ከንቲባው ከድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር ከድር ጁሃር በስልክ ባደረጉት ግንኙነት የተፈጠረው የእሳት ቃጠሎ ከልባቸው እንዳዘኑና በቀጣይ ከአስተዳደሩ ጎን እንደሚቆሙ አረጋግጠውላቸዋል፡፡

ከንቲባ አቶ ሰኢድ ዳውድ በስልክ መልዕክታቸው ‘’በድሬዳዋ ላይ ስለደረሰው የእሳት ቃጠሎ በመስማቴ በጣም አዝኛለሁ ፣ በዚህ አሳዛኝ ወቅት የጅቡቲ ከተማ አስተዳደር እና የጅቡቲ ዋና ከተማ ህዝብ ከጎናቹ መሆናችንን ልገልፅልህ እወዳለሁ” ብለዋል፡፡

አቶ ሰኢድ ዳውድ አክለውም በዚህ አሳዛኝ ሁኔታ የተጎዱት ከድሬዳዋ እህት ህዝብ ጋር ችግሩንና ጉዳታቸውን እንካፍላለን በዚህው አጋጣሚ አላህ የሰውን ህይወት ይጠብቅልን ብለዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *