የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅን አጸደቀ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 36ኛ መደበኛ ጉባኤ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅን አጽድቋል፡፡

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ በቋሚ ኮሚቴው የተዘጋጀውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡

አዋጁ ቁጠባንና ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት ትልቅ ሚና ያለውና የካፒታል ዕቃዎችን ሳይጨምር በዕቃ እና አገልግሎት ፍጆታ ላይ የተጣለ ስለመሆኑ በሪፖርቱ ተጠቁሟል፡፡

አዋጁ በታክስ ከፋዩ እና በታክስ ሰብሳቢው መስሪያ ቤት መካከል ሲፈጠር የነበረውን ያለመግባባት በማስወገድ ምቹ የሆነ የታክስ አስተዳደር እንዲኖር የሚያግዝ እንደሆነም ተመላክቷል፡፡

መንግስት ኢኮኖሚው ከሚያመነጨው ሃብት ተገቢውን ድርሻ እንዲያገኝ የሚያስችልና ከታክስ ነፃ መብት ገደብ የሚያበጅ አዋጅ እንደሆ አቶ ደሳለኝ ባቀረቡት የውሳኔ ሀሳብ አስረድተዋል፡፡

ምክር ቤቱ የተጨማሪ እሴት ታክስ ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት ካደረገ በኋላ አዋጅ ቁጥር 1341/2016 አድርጎ በሙሉ ድምጽ ማፅደቁን ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

EBC

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *