የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት በአስተዳደሩ ለረጀም ጊዜ በቀድሞ ማዘጋጃ ቤት በከተማው የደረቅ ቆሻሻ በማሰባሰብ እና በማስወገድ በባለቢጫዋ ማርቼዲስ መኪና የትራንስፖርት አገልግሎት ሲሰጡ ለነበሩት ለአቶ ጣሰው በዳዳ የአውቅና የምስጋና መርሀ ግብር በማዘጋጀት የዋናጫ እና የ100ሺ ብር የማበረታቻ ሽልማት ከድሬደዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር እጅ በዛሬው እለት ተበርክቶላቸዋል፡፡
አቶ ጣሰው በዳዳ በድሬዳዋ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ወይም ኮተኒ ለ27 አመት ፣ በከተማ ስራስኪያጅ በፅዳት እና ውበት ኤጀንሲ ለ21 አመት እንዲሁም በታክሲ ስራ ለ 7 አመት ሰርተዋል፡፡
አቶ ጣሰው በዳዳም አስተዳደሩ ልዩ ክብር በመስጠት ላደረገላቸው እውቅና እና ድጋፍ መደሰታቸውን ገልጸው ለክቡር ከንቲባው ምስጋና አቅርበዋል፡፡


