የአሰሊሶ ወረዳ ከድሬደዋ ወጣቶችና ስፓርት ኮምሽን ጋር በመተባበር በወረዳው ለሚገኙ 500 ወጣቶች የማነቃቂያና የህይወት ተሞክሮ ስልጠና ሰጥቷል።
የአሰሊሶ ወረዳ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አብዲ አበደላ ወጣቶች በአንድ አገር አጠቃላይ እድገትና መፃዒ የለውጥ ስኬት ትልቁን ድርሻ የሚወስዱ አምራች ሃይል እንደሆኑ አውስተዋል።በአስተዳደራችን ወጣቱን በሙሉ ሃይል በማህበራዊ ፓለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ መድክ ተሳታፊ ከመሆን ባለፈ ለሚኖረው ለውጥ ባለቤት እንዲሆኑ የሚያስችሉ ሰፊ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም ገልፀዋል።
ወጣቱ በተለይም የስራ ባህልና ፍቅሩ ተቀይሮና አድጎ እራሱንና ወገኑን የሚጠቅም አምራች ዜጋ መሆን አንደሚገባው የገለፁት አቶ አብዲ የአሰሊሶ ወረዳ ”የፍሪ ትረሌድ ዞንና የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡርን” ጨምሮ በርካታ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ አስቻይ ሁኔታዎች እናደሰሩ ጠቅሰዋል።
በመሆኑም እነዚህን ምቹ ሁኔታዎች ተጠቅመው ወጣቶች እራሳቸውን እንዲለውጡ ለማስቻል ጭምር ”በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል በ2016 ዓም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ” የስብዕና ልህቀት” የበጎ ፈቃደኞ ወጣቶች ስልጠናው መዘጋጀቱን ተናግረዋል።
ከቴክኖሎጂና ሌሎች ጎታች ሁኔታዎች እራሳቸውን ቆጥበው አልችልም ከማለት ይልቅ ለለውጥ የመነሳሳትን ፣ የግጭትና ከአለመግባባት ይልቅ ሰላምንና አንድነትን የሚያስቀድም ፣ ለችግሮች ሌሎችን ተጠያቂ ከማድረግ ይልቅ መፍትሄ አፍላቂ ዜጋ ለመሆን በአጠቃላይ እራስን ከነባራዊ ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ጋር በማዋሃድ በራሱ የሚተማመን ወጣት እንዲፈጠት መነሻ የግንዛቤ አቅም ለመፍጠር ስልጠናው እገዛ እንደሚያደርግ ታምኖበት መካሄዱን የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አብዲ አበደላ አብራርተዋለወ።
ወጣቶች አሁን ካለው አስተዳደራዊ አገራዊና አለማቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታ አንፃር እራሳቸው ያሉበት ደረጃና ሁኔታ መረዳትና ለለወጥ መነሳት እናዳለባቸው ስልጠናውን የሰጡት በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ የማነቃቂያ ንግግ በማድረግ የሚታወቁት ዶክተር ኢብሳ ደሚና ተናግረዋል።
ድሬዳዋ በፍቅርና አብሮ የመኖር መልካም እሴት የዳበረባት ከመሆኗ ባለፈ ሰርቶ ለመለወጥ የሚቻልባት እንደመሆኗ ወጣቱ ነገን ዛሬ ለመስራት በሙሉ አቅማቸው መንቀሳቀስ እንዳለባቸው ዶክተር ኢብሳ ጠቁመዋል።
እራስን በትምህርት ማጎልበት ዋናው የለውጥ ቁልፍ መሆኑን ወጣቶች በሚገባ መገንዘብ እንዳለባቸው የገለፁት ዶክተር ኢብሳ እንደዚህ ያሉ ስልጠናዎች ለመለወጥ የሚያስችል በእጅ ያለን ሃብት ለማውቅና ለመጠቀም የሚጥር በተስፋ የተሞላ ነገን አሻግሮ የሚያይ ወጣት ለመፍጠር ስለሚያግዝ መሰል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች መቀጠል እንዳለባቸው ገልፀዋል።
በስልጠናው ከዚህ ቀደም የማያውቋቸውን ፣ እያወቋቸውም ቢሆን በውል ያልተገነዘቧቸውን ጠቃሚ ሃሳቦችን ማግኝት መቻላቸውን በቀጣይም ለሌሎች አቻዎቻቸው ለማሳወቅ ዝግጁ መሆናቸውን በስልጠናው ከተሳተፈ ያነጋገርናቸው ወጣቶች ገልፀዋለወ።


