#DGC መስከረም 20/2017
በድሬዳዋ አስተዳደር በወረዳ 03 አካባቢ የኮሪደር ልማቱ በሚያልፍባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎችን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር አወያይተዋል።
በውይይቱ የተሳተፉ የወረዳ 03 የልማት ተነሺዎች ጥያቄዎቻቸውን ለከንቲባ ከድር ጁሀር አቅርበዋል፤ ድሬዳዋ ከተማ በልማት ወደኋላ ቀርታለች መልማት አለባት ፤ ልማቷ ግን ህብረተሰቧን ሊጎዳና ጎዳና ሊጥል በሚችል መልኩ መሆን የለበትም ፤ በልማቱ ምክንያት እንድንነሳ የተሰጠን የግዜ ገደብ በጣም አናሳ በመሆኑ በመጉላላት ላይ እንገኛለን በልማቱ ለሚነሱ ዜጎች ምን ታስቧል የሚሉት ከልማት ተነሺዎች የቀረቡ
ጥያቄዎች ናቸው ።
በውይይቱም ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከንቲባ ከድር ጁሀር በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ
ለተፈጠረው መጉላላት ይቅርታቸውን በመንግስት ስም ጠይቀው በሚካሔደው የኮሪደር ልማት ጎዳና ላይ የሚጣል ማህበረሰብ የለንም ሲሉ አረጋግጠዋል።
በመሆኑም መሬቱ የሚነካበት ግለሰብ ነዋሪ ምትክ ቦታ ተዘጋጅቷል ፤ በመንግስት ቤት ለሚኖሩት ቤታቸው ለፈረሰባቸው ምትክ ቤት እንደሚሰጣቸው ገልጸዋል።
ከንቲባው አክለውም የመልካ መንገድ ልማትን በተመለከተም እንደተናገሩት መንገዱ የሚነካቸው ቤቶችን የማፍረስና መንገዱን የመጥረግ ሒደቱ እንደሚካሔድ ተናግረዋል።
በድሬዳዋ የሚካሔደው የኮሪደር ልማት በመጀመሪያው ዙር የሚለሙት አካባቢዎች ከምድር ባቡር ክለብ እስከ ፍርድ ቤት ድረስ ፣ ከፍርድ ቤት እስከ ሰብሪያ ሞይንኮ ፣ ከነምበር ዋን ግብርና መገንጠያ እስከ ቬራ ፓስታ ድረስ እንዲሁም ቤት የማፍረሱ ሒደት እስከ አኳ ኡኖ እንደሚቀጥልና የለገሀሬው የመንገድ ከፈታውም ስራም እንደተጀመረ ከንቲባ ከድር ጁሀር በውይይቱ በቅት ገልፀዋል።
ምንጭ፦dire tv
ምስል:- አብይ ሽመልስ


