የድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት በታሪፍ ማሻሻያ ባወጣው ረቂቅ መመሪያ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እካሄደ
የድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት የመኝታ አገልግሎት ግብር አሰባሰብ አመዘጋገብና የሪፖርት አቀራረብ መመሪያ ቁጥር 1703/2017 ላይ በዛሬው እለት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል:: በውይይት መድረኩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ኃላፊ ኢንጂነር ጀማል ኢብራሂም በዛሬው መድረክ በዋነኝነት የመኝታ ግብር ለማሰባሰብ በወጣው ረቂቅ መመሪያ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየትና ግብአት በማሰባሰብ…


