ድሬዳዋ ከተማ ወላይታ ድቻን በማሸነፍ የሊጉ መሪ ሆኗል

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማ ወላይታ ድቻን 4 ለ 1 አሸንፏል።

በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዩጋንዳዊው ቻርልስ ሙሲጌ እና መሐመድ ኑር ናስር በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን ለድሬዳዋ ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ያሬድ ዳርዛ ለወላይታ ድቻ በ75ኛው ደቂቃ ብቸኛዋን ግብ አስቆጥሯል።

ውጤቱን ተከትሎ ድሬዳዋ ከተማ በስድስት ነጥብ የሊጉ መሪነት ይዟል።

ተጋጣሚው ወላይታ ድቻ በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

ቀን ላይ በተደረገ ጨዋታ ሲዳማ ቡና መቻልን 2 ለ 1 አሸንፏል። ጨዋታዎቹን ተከትሎ የሁለተኛ ሳምንት የሊጉ መርሃ ግብር ተጠናቋል።

የሶስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከሰኞ መስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም አንስቶ እንደሚካሄዱ የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *