በዛሬው እለት ማለትም ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም የተጀመረውና የብልፅግና ፓርቲ አባል ለሆኑ የመንግስት ሰራተኞች የሚሰጠው ስልጠና በዋናነት የብልፅግና ፓርቲ አባላትን የግንዛቤ አድማስ የሚያሰፋ ከመሆኑም በላይ ለቀጣይ የልማት ስራዎች እና ለሀገራዊ ሁለንተናዊ ብልፅግና ስኬት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲወጡ የሚያግዝ ነው ።
ከዚህ በተጨማሪም የብልፅግና ፓርቲ ያለፉት አምስት ዓመታት በተለይም በፖለቲካ ፣ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የተሰሩ በርካታ ስራዎች እንዲሁም የሰላም እና የልማት ስኬታማ ጉዞዎች የሚዳሰስበትም ይሆናል ። ስልጠናዉም ዛሬ እና ነገ የሚሰጥም ይሆናል ።
በአለማየኩ አበበ ።
ፎቶ :- በሰላም አበበ ።


