የብልፅግና ፓርቲ 4ኛው ዙር “የህልም ጉልበት ለእምርታዊ እድገት” ስልጠና ለከንቲባ ፅ/ቤትና ለተለያዩ ተቋማት ለመሠረታዊ ድርጅት ኣባላት ስልጠና መስጠት ተጀመረ ።

#DGC ጥቅምት 29/2017

በአስተዳደሩ ለከንቲባ ጽ/ቤትና በስሩ ለሚገኙ ተቋማት አባላት በተዘጋጀው ስልጠና ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደርጉት የከንቲባና የካቢኔ ጉዳዮች ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ገበየሁ ጥላሁን ብልፅግና ፓርቲ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ አካታች፣አሳታፊና ሁሉንም ዓይነት ኢትዮጵያዊ ብዝሃነትን ይዞ የተፈጠረ አገራዊ ህብረ-ብሔራዊ ፓርቲም ነው ብለዋል።

ከተመሠረተ ገና አጭር ጊዜ ቢሆንም መጠነ ሰፊ የሪፎርም ሂደት ውስጥ የሚገኝና ዓይነተ ብዙ ዕመርታ እያስመዘገበ ያለ ታላቅ አፍሪካዊ ፓርቲ ነው ያሉት አቶ ገበየሁ ባሳለፍናቸው አምስት ዓመታት ገና ከምስረታው ጀምሮ በርካታ ፈተናዎች ያጋጠሙት ቢሆንም እነዚህን ሰው ሠራሽና የተፈጥሮ ፈተናዎች በመቋቋም በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚው፣ በማህበራዊና በዲፕሎማሲው ዘርፎች በርካታ ድሎችን ማስመዝገብ የቻለ ፓርቲ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ብልፅግና ለፈተናዎች ያልተንበረከከ ፈተናን ወደ ዕድል የመቀየር ብሂልና ልምድ እያካበተ የመጣ ፈጠራና ፍጥነትን ማዕከል አድርጎ የሚንቀሳቀስ ፓርቲ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የፓርቲው አገራዊ ውጥኖቹ የተሳኩ ይሆን ዘንድ

የአመራሩና አባሉን የአመለካከትና የአስተሳሰብ አንድነት ማረጋገጥ ይቻል ዘንድ እንዲሁም አገራዊ የለውጥ ሂደቱ በጀመረበት ግለት ለሰከንድ ሳይንቀረፈፍ በፍጥነት ማስቀጠል አስፈላጊ በመሆኑ ይህንኑ በብቃት ለመምራትና ዳር ለማድረስ በየጊዜው የአመራሩን እና የአባላቱን አቅም መገንባት በእጅጉ አስፈላጊ በመሆኑ ይህ ስልጠና አስፈልጓል ብለዋል።

ስልጠናው በሶስት ምዕራፍ የተከፋፈለ ሲሆን በመጀመረያው “የህልም ጉልበት ለእምርታዊ እድገት “ስልጠና፣ የአምስት አመት ጉዞና የተገኙ ውጤቶች እንዲሁም የተገኙ ውጤቶችን ማስቀጠል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ነው ስልጠናው እየተሰጠ ያለው ::

Dire tv

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *