ድሬ ቪአይፒ ጤና ቡድን ከ ድሬ ጤና ቡድን በዛሬው እለት የእግር ኳስ ጨዋታቸውን በድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ያካሄዱ ሲሆን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር ለድሬ ቪአይፒ ጤና ቡድን ፣ አክሊል በድሩ እና ቢኒያም ይትባረክ ለድሬ ጤና ቡድን ባስቆጠሯቸው ጎሎች 2 ለ 2 በሆነ ውጤት ጨዋታው አልቋል ።
ከዚህ ቀደም ድሬ ቪአይፒ ጤና ቡድን ከ ድሬ ጤና ቡድን ጋር በነበራቸው ጨዋታ ድሬ ቪአይፒ ጤና ቡድን ፣ ድሬ ጤና ቡድንን 6 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ አይዘነጋም ። የዛሬው ጨዋታም 2 ለ 2 በሆነ ውጤት በማለቁ ምክንያት በአጠቃላይ ውጤት 8 ለ 2 አልቋል ። በዚህም ድሬ ቪአይፒ ጤና ቡድን የዋንጫ ተሸላሚ መሆን ችሏል ።
ድሬ ቪአይፒ ጤና ቡድን 36 ተኛ ጨዋታውን ነው በዛሬው እለት ማድረግ የቻለው ።
በአለማየሁ አበበ ።
ምስል :- በአገኘው ሸዋረጋ እና ቴዎድሮስ ልኡልሰገድ ።


