የደቡብ ሱዳን የግብርና እና የምግብ ዋስትና ሚኒስቴር ሚኒስትር ፣ የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራምን የሚደግፍ ከልማት ተቋማት የመጡ የኔዘርላንድ ምክትል አምባሳደር ፣ የአይሪሼድ የፕሮግራምን የሚደግፍ አጋር ድርጅት እና ፕሮግራም ሀላፊዎች ፣ የብሪቲሽ ኤምባሲ ፕሮግራም ሀላፊ ፣ ከገንዘብ ሚኒስቴር ፣ ከግብርና ሚኒስቴር እንዲሁም ከማህበራዊ ጉዳይ የመጡ ባለሞያዎች በዛሬው እለት ድሬዳዋ ገብተዋል ።

ድሬዳዋ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሀርቢ ቡህ ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር የግብርና ውሀ ማእድንና ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊ አቶ ኑረዲን አብደላ እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ከድር አሊይ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *