የደቡብ ሱዳን የግብርና እና የምግብ ዋስትና ሚኒስቴር ሚኒስትር ፣ የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራምን የሚደግፍ ከልማት ተቋማት የመጡ የኔዘርላንድ ምክትል አምባሳደር ፣ የአይሪሼድ የፕሮግራምን የሚደግፍ አጋር ድርጅት እና ፕሮግራም ሀላፊዎች ፣ የብሪቲሽ ኤምባሲ ፕሮግራም ሀላፊ ፣ ከገንዘብ ሚኒስቴር ፣ ከግብርና ሚኒስቴር እንዲሁም ከማህበራዊ ጉዳይ የመጡ ባለሞያዎች በዛሬው እለት ድሬዳዋ ገብተዋል ።

ድሬዳዋ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሀርቢ ቡህ ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር የግብርና ውሀ ማእድንና ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊ አቶ ኑረዲን አብደላ እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ከድር አሊይ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

Read More

ድሬ ቪአይፒ ጤና ቡድን በአጠቃላይ ውጤት 8 – 2 አሸናፊ ሆነ ።

ድሬ ቪአይፒ ጤና ቡድን ከ ድሬ ጤና ቡድን በዛሬው እለት የእግር ኳስ ጨዋታቸውን በድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ያካሄዱ ሲሆን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር ለድሬ ቪአይፒ ጤና ቡድን ፣ አክሊል በድሩ እና ቢኒያም ይትባረክ ለድሬ ጤና ቡድን ባስቆጠሯቸው ጎሎች 2 ለ 2 በሆነ ውጤት ጨዋታው አልቋል ። ከዚህ ቀደም ድሬ ቪአይፒ ጤና ቡድን ከ…

Read More