በድሬዳዋ አስተዳደር ከለውጡ መንግስት በኋላ የተሰሩ የልማት ስራዎች ተጎበኙ::

#DGC ህዳር 10/2017

የብልፅግና ፓርቲ 5 ተኛ አመት የምስረታ በዓልን አስመልክቶ ባለፍት ቀናት በድሬዳዋ አስተዳደር በተለያዩ መርሀ-ግብሮች እየተከበረ ይገኛል ። በዛሬው እለትም በድሬዳዋ አስተዳደር ባለፍት አምስት አመታት የተሰሩ የልማት ስራዎች ተጎብኝቷል ።

በዛሬው እለትም የተጎበኙት የኢትዮጲያ ፕሪሚየር ሊግን እያስተናገደ ያለው የድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ፣ ከለውጡ ማግስት በርካታ የሪፎርም ስራዎችን መስራት የቻለው የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ፣ የተለያዩ የታሸጉ ውሀዎችን የሚያመርተው አኳ ኡኖ የውሀ ፋብሪካ እንዲሁም የተለያዩ መኪናዎችን የሚገጣጥመው ኤኤም ሞተርስ ናቸው ።

በዛሬው እለት በአስተዳደሩ ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ያሉ የልማት ስራዎች ሲጎበኙም በተለይም የድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ውስጥ ያሉትን አጠቃላይ መረጃዎች የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር ለጉብኝቱ ላይ ለተሳተፍት ገለፃ አድርገዋል ። ከዚህም በተጨማሪ በአስተዳደሩ ከለውጡ መንግስት በኋላ በተቋማት እየተሰሩ ያሉ የሪፎርም ስራዋች እና የልማት ስራዋችን አጠናክረን የምናስቀጥል ይሆናል ሲሉም ተናግረዋል።

ባለፍት ቀናትም የብልፅግና ፓርቲ 5 ተኛ አመት የምስረታ በዓልን አስመልክቶ በድሬዳዋ አስተዳደር ላይ በተለያዩ መርሀ-ግብሮች እየተከበረ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር የስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ተናግረው በዛሬው እለትም ባለፍት አምስት አመታት በአስተዳደሩ ላይ የተሰሩ የተለያዩ የልማት ስራዎች እንደተጎበኙና እነዚህንም የልማት ስራዎች ነዋሪው ህብረተሰብ በተጨባጭ እንዲያውቃቸው ለማስቻል ታስቦ የጉብኝት መርሀ-ግብሩ መዘጋጀቱንም ነው አቶ ሮቤል ጌታቸው ያስታወቁት ።

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር ጆሀር በመሩት የልዑካን ቡድን የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር አለሙ መርጋ ፣ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የመንግስት ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል ።

በአለማየሁ አበበ

ፎቶ ፦ በአገኘሁ ሸዋረጋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *