#DGC ህዳር 10/2017
“የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሀሳብ የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ አመት የምስረታ በዓልን አስመልክቶ በርካታ መርሀግብሮች በአስተዳደሩ እየተከናወነ መሆኑ ይታወቃል በዛሬውም እለት በአስተዳደሩ ተግባራዊ የሆኑ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ጉብኝት ተካሂዷል።
በጉብኝቱም የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የንግድ ኢንዱስትሪ ና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ በክቡር አቶ ሀርቢ ቡህ የሚመራዉ ምድብ የሲቪክ ማዕከል የግንባታ ፕሮጀክትን ጓብኝቷል።
በአስተዳደሩ የኢኮኖሚ ሪፎርም ከማረጋገጥ አንጻር በተለይም በራስ አቅም በአስተዳደሩ ወጪ ከሚተገበሩ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች የሲቪክ ማዕከል ግንባታው አንድ ሲሆን የፕሮጀክቱ ግንባታ ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ የከተማዋን ደረጃ በማሳደግ ለኮንፍረንስ ቱሪዝም ማዕከል ቁልፍ ሚና እንደሚኖረው ምክትል ከንቲባ ክቡር ሀርቢ ቡህ ገልጸዋል።
በሲቪክ ማዕከሉ ውስጥም ከ2ሺ በላይ ማስተናገድ የሚችል የስብሰባአዳራሽ፣ሙዚየም፣ካፍቴሪያ፣ቤተ-መጽሀፍት እና ልዩ ልዩ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ አዳራሾች ይገኙበታል።
በሰላም ለማ
ምስል፦ ረመዳን አደም


