የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚተገበሩ ፕሮጀክቶች ስኬታማ እንዲሆኑ አስፈላጊ የክትትልና ግምገማ ስርዓት መዘርጋትና የባለድርሻ አካላት ቅንጅት እንደሚጠይቅ ተገለፀ::

#DGC ህዳር 8/2017

በፕሮጀክት አስተዳደር እና ውጤታማ የፕሮጀክት ክትትልና ግምገማ ስርዓት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሂዷል።

በአስተዳደሩ በተለይም ተፈጥሮን መሰረት ያደረጉ የተፈጥሮ ሃብትጥበቃና እንክብካቤ የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ፕሮጀክቶች መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት ይከናወናሉ።

በዚህ ረገድ በአስተዳደሩ የከተማና ገጠር አካባቢዎች የሚተገበረው የSUNCASA /Scaling Urban Nature Based Solution for Climate Adaptation in Sub-Saharan Africa/ አንዱ ሲሆን የፕሮጀክቱ ትግበራ የተፈለገለትን አላማ ማሳካት እንዲችል በፕሮጀክቱ የሚሳተፉ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ህዝቡን ያቀናጀ የተጠናከረ አሰራር መተግበር እንደሚገባ የድሬደዋ አስተዳደር አከባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን ሃላፊ አቶ አብዱ መሃመድ በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ገልፀዋል።

ስልጠናው በቀጣይ ፕሮጀክቱ ትግበራ ላይ ሊከናወኑ የሚገባቸውን የክትትልና ግምገማ ስራዎች እንዲሁም የተሻለ አፈጻጸም እንዲኖር ጉልህ ሚና እንደሚኖረው አቶ አብዱ መሃመድ ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱን በተሻለ ለመተግበር የሚያስችል በፕሮጀክት አስተዳደር /Project Management/ እና ውጤታማ የፕሮጀክት ክትትልና ግምገማ ስርዓት /Result based Project Monitoring and Evaluation/ ዙሪያ ለፕሮከጀቱ ባለድርሻ አካላት የድሬዳዋ አስተዳደር አካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን የአቅም ግንባታ ስልጠና እንዲሰጥ መደረጉን ሃላፊው ገልፀዋል።

በስልጠናው ፕሮጀክቱን ከሚተገብሩት የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ፣ የሐረርጌ ካቶሊክ ሴክሬተሪያት እንዲሁም የግብርና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ፣ የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ፣ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ፣ የፕላንና ኢኮኖሚ ልማት ኮሚሽን፣ የጽዳትና ውበት ኤጀንሲ፣ የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን እና የባለስልጣን መ/ቤቱ ባለሙያዎችና አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *