በድሬዳዋ አስተዳደር ቢዮአዋሌ ክላስተር ለገቢራ ገጠር ቀበሌ የደረሱ የአርሶ አደር የማሽላ ሰብሎች ተሰበሰቡ::

#DGC ህዳር 15/2017

በድሬዳዋ አስተዳደር የ 2017 የምርት ማሰባሰብ ንቅናቄ በቢዮ አዋሌ ክላስተር ለገቢራ ገጠር ቀበሌ የተካሄደ ሲሆን የደረሱ የማሽላ ሰብሎችም ተሰብስበዋል ።

በዛሬው እለትም ከ 200 በላይ የፀጥታ አካላት ተሳታፊ ከመሆናቸውም በላይ ሰራዊቱ የሀገራቸውን ሰላም እና ፀጥታ ከማስጠበቅ ጎን ለጎን ከወገኖቻቸው ጎን መሆናቸውን በተጨባጭ ማሳየት መቻላቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር ተናግረው በዛሬው እለት የተካሄደው የማሽላ ቆረጣም በዋናነት ዝናብ እንዳያበላሸው እንዲሁም መሬቱን ለቀጣይ ዝግጁ ለማድረግ ታስቦ ሰብሎቹ መሰብሰባቸውን ክቡር አቶ ከድር ጁሀር ተናግረዋል።

እንደ አስተዳደር አርሶ አደሩ ላይ የግብርና ልማት ስራዎች በስፋት እየተሰሩ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር የግብርና ውሀ ማእድንና ኢንጂነር ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ኑረዲን አብደላ ተናግረው በተለይም አርሶ አደሩ እርጥበቱን ተጠቅሞ ምርጥ ዘርን በመጠቀም በያዝነው አመት ይገኛል ተብሎ ከሚጠበቀው ምርት አንፃር በተደረገ የቅድመ ዳሰሳ የምርት ጥናት ከ 97 ፐርሰንት በላይ ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅም ነው አቶ ኑረዲን ያስታወቁት ።

በማሽላ አጨዳው ላይም የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር ፣ በብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ፣ የአስተዳደሩ የካቢኔ አባላት ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ፣ የፌደራል ፓሊስ ፣ የድሬዳዋ ፓሊስ ፣ የኢ.ፌ.ድ.ሪ አየር ሀይል የምስራቅ አየር ምድብ አመራር እና አባላት እንዲሁም አርሶ እና አርብቶ አደሮች ተገኝተዋል ።

በአለማየሁ አበበ

ፎቶ :- ረመዳን አደም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *