ለውጡና የለውጡ ፍሬዎች

በሕዝብ ግፊትና በፓርቲ ሳቢነት የመጣው ሀገራዊ ለውጥ፣ የመጀመሪያውን ምእራፍ እየተሻገረ ነው፡፡ በዚህ የመጀመሪያ ምእራፍ የለውጡን ሐሳቦች በቃልና በተግባር ተገልጠዋል፡፡ የለውጡ ፈተናዎችም አካል ገዝተው በሚገባ በመገለጣቸው ሕዝብ ዐውቆ እንዲታገላቸው ተደርጓል፡፡ ይሄም የለውጡን ፍሬዎች ለማጎምራት፣ የለውጡን ፈተናዎችንም ለመርታት ዕድል ሰጥቷል፡፡

ባለፉት ስድስት ዓመታት በኢትዮጵያ ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ ሲጠየቁ የነበሩ ጥያቄዎች ከቃል አልፈው ተግባራዊ ምላሽ አግኝተዋል፡፡ የፖሊሲ፣ የሕግ እና የአሠራር ብቻ ሳይሆን የባህል ለውጥ አምጥተዋል፡፡ ለውጡ ያለፉት የሀገሪቱን ስብራቶች የሚጠግን፣ ዛሬን የሚዋጅና የነገውን የኢትዮጵያ ጉዞ የሚያቀና ነው፡፡ የለውጡ ዘመን መሪ ፓርቲ የሆነው ብልጽግና አምስተኛ ዓመቱን በሚያከብርበት በዚህ ወቅት የሚከተሉትን አንኳር የለውጥ ውጤቶች ማንሣቱ ተገቢ ነው፡፡

የብልጽግና መመሥረት፡

የኢትዮጵያ ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ የፖለቲካ ፓርቲዎች ታሪክ ነው፡፡ እነዚህ የፖለቲካ ፓርቲዎች የፖለቲካ ንቃት በማኅበረሰቡ ውስጥ እንዲፈጠር አድርገዋል፡፡ የፖለቲካ አደረጃቶችን አምጥተዋል፡፡ የሕዝብ ጥያቄዎችን ቅርጽና መልክ ሰጥተዋል፡፡ የፖለቲካ ትግል ስልቶችንም አስተዋውቀዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የትጥቅ ትግልና የፖለቲካ ትግል እንዲቀላቀል፤ የጥላቻ ፖለቲካ እንዲነግሥ፣ በብሔር፣ በርዕዮተ ዓለምና በትግል ስልት መፈራረጅ እንዲበረታ በማድረግ ለዘመናዊ የፖለቲካ ጉዟችን ሳንካዎችን አኑረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *