የፌደራል ፣ የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የገቢ ተቋማት የ4 ወራት የገቢና የዋና ዋና ስራዎች እቅድ አፈፃፀም ግምገማ የጋራ ምክክር መድረክ ተሳታፊዋች በድሬዳዋ አስተዳደር እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዋችን ጎበኙ

#DGC | ህዳር 17/2017

በጉብኝት መርሀ ግብሩም የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ እንዲሁም ሌሎች የሚኒስቴሩ፣የክልልና የከተማ ቅ/ጽ/ቤት አመራሮች ተገኝተዋል።

በዚህም በጉብኝታቸው የድሬዳዋን ኢንተርናሽናል እስታዲየምን፣ ነፃ የንግድ ቀጠናን እንዲሁም የሲቪክ ሴንተርን ተመልክተዋል።

የፌደራል ፣ የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የገቢ ተቋማት የ4 ወራት የገቢና የዋና ዋና ስራዎች እቅድ አፈፃፀም ግምገማ የጋራ ምክክር መድረክ በድሬዳዋ አስተዳደር በትላንትናው እለት መካሄድ መጀመሩ የሚታወስ ሲሆን፤ በዛሬው እለትም በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በክብርት ወይዘሮ አይናለም ንጉሴ ማጠቃለያና ቀጣይ የስራ አቅጣጫ ተሰቷል።

በኤደን ሳሙኤል

ፎቶ:- አገኘሁ ሸዋረጋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *