በድሬዳዋ አስተዳደሩ ለውጡን ተከትሎ በትራንስፖርት ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶች አበረታች መሆናቸው ተገለፀ።

#DGC | ህዳር / 2017 ዓ.ም

በአስተዳደሩ ለውጡን ተከትሎ በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶች ለሀገራዊ ብሎም ለአስተዳደሩ እድገት የሚኖራቸው አበርክቶ ከፍተኛ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ክብርት ወ/ሮ ሽኩሪ አቡድረህማን በዛሬው እለት ከመንግስት ኮሙኒኬሽን ጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ አስታውቀዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክ ባለስልጣን በ2016 በጀት አመት የላቀ የስራ አፈጻጸም በማስመዝገብ በሀገር አቀፍ ደረጃ መሸለሙንና የዚህም ስኬት መመዝገብ የለውጥ አመራሩ እና የባለሰልጣን መስሪያቤቱ ሰራተኞች የትጋት ውጤት መሆኑን ተናግረዋል።

የትራንስፖርት ዘርፉን በተሻለ ሁኔታ ለመምራት የሚያስችል የአሰራር እና የህግ ማሻሻዎች መደረጋቸውና አዳዳስ የህግ ማእቀፎች ማዘጋጀቱ፣ በዘርፉ የዲጂታላይዜሽን ስራ የኢ ትኬቲንግ፣ኢ ፋይል እና ኢ ሰርቪስ አገልግሎት ተግባራዊ እተደረገ መሆኑን አብራርተዋል።

በቀጣይም በአስተዳደሩ ከከተማ እድገት ጋር በተያያዘ እየተስተዋለ ያለውን የትራንስፖርት እጥረት ለመቅረፍም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋት በትኩረት እንደሚሰራ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ዋና ስራ አስፈፃሚ ክብርት ወ/ሮ ሽኩሪ አቡድረህማን ገልጸዋል።

በሰላም ለማ

ምስል:- ረመዳን አደም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *