በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ትውልደ ድሬዳዋ ዲያስፖራዎችን ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ የሚያግዝ የቤት ለቤት መረጃ አሰባሰብ እንደሚሰራ ተገለፀ

#DGC ህዳር 19/2017

በድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የዲያስፖራ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት በዲያስፖራ ማፒንግ እና ፕሮጀክት ማኔጅመንት ስራ በውጪ ሀገራት የሚኖሩ ትውልደ ድሬዳዋ ዲያስፖራዎችን የቤት ለቤት ምዝገባ፤ በከተማ እና በገጠር ወረዳዎች መረጃ ለመሰብሰብ እና ለማደራጀት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በዛሬው እለት የውይይት መድረክ አካሂዷል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት በከንቲባ ፅህፈት ቤት የዲያስፖራ ማስተባበሪያ ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ቢንያም ግርማ እንዳሉት በውጭ አገራት የሚኖሩ የድሬዳዋ ተወላጆችና ወዳጆችን ቅንጅታዊ አሰራርን በማሳደግ ዙሪያ እንዲሁም የዲያስፖራ የመኖሪያ ቤት ፖኬጅ ላይ ውይይት መደረጉን ጠቅሰው፤ የዲያስፖራውን ማህበረሰብ የተግባቦት ክፍተቱን ለመፍታት በቀላሉ ፈጣን መረጃዎችን ማግኘት የሚያስችል አሰራር መዘርጋቱን ገልፀዋል።

እነዚህን እንቅስቃሴዎች የበለጠ ለማሳደግ ዲያስፖራው የተቀናጀና ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኝ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑንም ገልጸዋል።

በውጪ ሀገራት የሚኖሩ ትውልደ ድሬዳዋ ዲያስፖራዎችን የቤት ለቤት ምዝገባ፤ በከተማ እና በገጠር ወረዳዎች መረጃ ለመሰብሰብ የሚያስችል ውይይት የተደረገ ሲሆን የዳያስፖራውን ማህበረሰብ አገራዊ የልማት ተሳትፎ በላቀ ደረጃ ለማሳደግ ጥሩ መደላድል እንደሚፈጥርለትም አቶ ቢንያም ገልጸዋል።

በድሬዳዋ የዲያስፖራው ማህበራዊ ልማት እና ኢንቨስትመንት ተሳትፎ እንዲያድግ የሚያግዙ አሰራሮች እየተዘረጉ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ቢንያም በተጨማሪም የዲያስፖራውን የተደራጀ መረጃ ለመሰብሰብ የሚያስችል አዲስ የበለጸገ ሶፍትዌር ተግባራዊ እንደሆነም ነዉ በመድረኩ ያብራሩት።

መድረኩ በዋናነት በውጪ ሀገራት የሚኖሩ ትውልደ ድሬዳዋ ዲያስፖራዎችን በተደራጀ መልኩ በድሬዳዋ ልማት እንዲሳተፉ ለማድረግ እንዲሁም በቀጣይ የዲያስፖራ ፖሊሲዎች እና ስትራቴጂዎችን ተግባራዊ ለማድረግ በሚደረገው የቤት ለቤት መረጃ አሰባሰብ ላይ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው የድሬዳዋ አስተዳደር የዲያስፖራ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ቢንያም ግርማ አስረድተዋል።

በበድሉ ሀይሌ

ፎቶ:- አገኘሁ ሸዋረጋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *