#DGC ህዳር 26/217
የድሬዳዋ አስተዳደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ከአስተዳደሩ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ጋር በመተባበር በዳኝነት ዲጂታላይዜሽን እና መሰረተ ልማት፣ በኢ-ኮርት ኬዝ ማኔጅመንት ሲስተም፣ በኤሌክትሮኒክስ መዛግብት አስተዳደር ስርአት እንዲሁም በemerging technology ዙሪያ በአስተዳደሩ ለሚገኙ ፍርድ ቤት ዳኞችና ባለሞያዎች ስልጠና መስጠት ጀመረ ፡፡
በዚህም በመድረኩ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፈቲያ አደን ለሰልጣኞች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን በማስተላለፍ የፍትህ ተቋማትን አሰራር በማጠናከርና በማዘመን የተገልጋዮችን እርካታ መጨመር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ክብርት ወ/ሮ ፈቲያ አያይዘውም የፍርድ ቤቶች እስማርት ኮርት ሩም አሰራርን መተግበራቸው ፈጣንና ግልፅ የፍርድ ሂደት እንዲኖር እንደሚያስችልም ክብርት አፈ-ጉባኤዋ ተናግረው፤ የስልጠናው ተሳታፊዎች ትኩረት ሰተው እንዲከታተሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት የሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ አብዱለዚዝ ሻፊ በበኩላቻ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በሰጡት አቅጣጫ መሰረት የተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶችን አሰራር የማዘመን ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
አቶ አብዱለዚዝ አያይዘውም በአጠቃላይ የፍትህ አሰጣጥ ሂደቱን ለማቀላጠፍና ስማርት ኮርት ሩምን ተግባራዊ ለማድረግ ብሎም ለማህበረሰቡ የተቀላጠፈ አገልግሎቶችን ለመስጠት በርብርብ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ነጂብ ኢድሪስ በበኩላቸው ኮርት ኬዝ ማኔጅመንት ሲስተምን ዌብ ቤዝ ለማድረግና ፍርድ ቤት የኢ-ፋይሊንግ ስርአትን ለመተግበር እንዲሁም የዳሽ ቦርድ ሲስተምን ለመዘርጋትና እስማርት ኮርት ሩም ለመገንባት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
በኤደን ሳሙኤል


