በዚህም በመድረኩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ተወካይ እና የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገበየሁ ጥላሁን ድሬዳዋ ላይ በስፖርቱ ዘርፍ በርብርብና በቅንጅት እየተሰራ ያለው ስራ የሚያበረታታ መሆኑን ተናግረው ይህም በቀጣይ ተጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል::
የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት እና የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ በበኩላቸው ለእንግዶች የእንኳን ደና መጣችሁ መልዕክታቸውን በማስተላለፍ በ2016 ዓ.ም የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በርካታ ስራዎችን እንደሰራ ገልፀዋል::
የ2016 ዓ.ም የዲቪዚዎን ጨዋታዎች በሰላምና በፍቅር እንደተጠናቀቁም ኮምሽነር አለሙ በመግለፅ ስራዎች በስኬት እንዲከናወኑ ከእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ጎን በመቆም ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል::
በቀጣይም በ2016 ዓ.ም የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል አንዳንድ የታዩ ክፍተቶች ላይ ተተኩሮ እንደሚሰራ ኮሚሽነር አለሙ ተናግረዋል: :
በመድረኩ የፌደሬሽኑ የ2016 ዓ.ም የስራ አፈፃፀም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን ከፌዴሬሽኑ ጋር በጋራ በመስራት የበኩላቸውን አስተዋፆ ላበረከቱ አካላት የሰርተፍኬት ሽልማት ተበርክቷል::


