የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ የድሬዳዋ የኮሪደር ልማት የስራ ሂደትን በተመለከተ ሳምንታዊ ግምገማ አድርገዋል::

#DGC ህዳር 27/2017

በግምገማው እያንዳንዱ ኮንትራክተር ለመስራት ባወጣው ሳምንታዊ የስራ መርሀ-ግብርን ተከትሎ ምን አከናወነ የሚለው ላይ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፤ በስራ ወቅት ባጋጠሙ አንዳንድ ችግሮች ላይም ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

በዚህም በሳይት የሳይክል መሄጃን መስመር ለመስራት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በመድረኩ ስራዎች በጥሩ ሁኔታ እየተሰሩ እንደሚገኙ ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ ገልፀው፤ በቀጣይም ስራዎችን በጥራትና በፍጥነት የመስራት ሂደት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።

በመድረኩ ማጠቃለያም ክቡር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ቀጣይ የስራ አቅጣጫን አስቀምጠዋል።

በኤደን ሳሙኤል

ፎቶ:- አገኘሁ ሸዋረጋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *