ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር በተገኙበት በቀረበው ሪፖርት ላይ የ2017 በጀት አመት የ4 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም 61.6 በመቶ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በድሬዳዋ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ከግብ ለማድረስ፥ ገቢ ወሳኝ መሆኑን በግምገማ መድረኩ ላይ የገለፁት የአስተዳደሩ ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር፥ በገቢ አሰባሰቡ ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸው ተቋማት በቀጣይ በስፋት መስራት እንዳልባቸው አሳስበዋል።
ተቋማት የገቢ አሰባሰቡን ለማሳደግ በቅንጅት መስራት እንዲሁም ያላቸውን አቅም አሟጠው መጠቅም እንዳለባቸው አጽንኦት የተሰጠበት ሲሆን፡፥ ለአስተዳደሩ ልማትና እድገት ወሳኝ ለሆነው የገቢ አሰባሰብ፥ ከተቋማት በተጨማሪ ሌሎች ባለድርሻ አካላትም ሊረባረቡ ይገባል ተብሏል፡፡
በግምገማ መድረኩ ማጠቃለያ የድሬዳዋ አስተዳደር የማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ አሰባሰብ የእቅድ አፈፃፀም በቀጣይ በየወሩ እንዲገመገም አቅጣጫ ተቀምጧል።
ምንጭ፦ድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት


