“ደቡብ ኢትዮጵያን መጎብኘት እና እንደ አርባምንጭ ያሉ ከተሞችን እድገት መመልከት ሁልጊዜም አስደሳች ነው!!” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

እንደ ሀገር የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ለከተሞችም ሆነ ለገጠር አካባቢዎች ፈተና ሆኖ የቀጠለ ጉዳይ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ በመጎብኘት ላይ እንዳለነው አይነት የሙዝ ልማት ሥራዎችን በገጠር አካባቢዎች በማሳዎች ላይ የኩታ ገጠም እርሻ አሰራረን ጀምረናል ብለዋል።

እነዚህን ጥረቶች የሚደግፈው የሌማት ትሩፋት ሥራ በየአርሶአርብቶአደሩ ቤት የእንቁላል ምርትን ከአሳ እና ከብት ርባታ ብሎም ንብ ማነብ ጋር ምርት በማሳደግ ላይ እንደሚገኝም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

እነዚህ መርሃግብሮች በጥምር የገጠሩ እና የከተማው ነዋሪዎች ከትሩፋቱ እንዲካፈሉ አልመው ሰርተዋል። በተለይ የኩታ ገጠም እርሻ በአርባምንጭ ታላቅ ተስፋ የሰነቀ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልእክታቸውን በማህበራዊ ሚዲያቸው አስተላልፈዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *