በድሬዳዋ አስተዳደር የከንቲባ ፅ/ቤት በ2017 በጀት አመት የሚተገበር የአስተዳደሩ የተጠቃለለ የሀብት መረጃ ማደራጀት የካቢታል ፕሮጀክት ማስጀመሪያ ሰነድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ ፡፡
ለድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ በኢኮኖሚ እና መሰረተ ልማት አማካሪ ደ/ር ፍቃዱ በየነ በውይይት መድረኩ እንደተናገሩት የማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ በወረዳ 02 እና 04 እንደሚጀመር በመግለፅ ወደ መሬት ወርዶ ተግባራዊ ሲሆም ለኢንቨስትመንት ፣ለውሳኔ አሰጣጥ፣ የማህበረሰቡን ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠትና የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት እንዲሁም ውጤታማ ክትትል ለማድረግ የጎላ ጠቀሚታ አለው ብለዋል፡፡
በድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ማዘጋጃቤታዊ ሀብት (የመሬት እና የመሬት ነክ )ተዛማጅ መረጃ አሰባሰብ ላይ ያተኮረ የመወያያ ሰነድ ለባለድርሻ አካላቶች የቀረበ ሲሆን በቀረበው የውይይት ሰነድ ላይም ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
በትዕግስት ቶሎሳ


