39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔና የጣሊያን አፍሪካ ጉባዔ በስኬት መጠናቀቃቸውን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታወቀ
በአዲስ አበባ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤና 2ኛው የጣሊያን አፍሪካ ጉባዔ በስኬት መጠናቀቃቸውን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታውቋል፡፡ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይሉ ለኢቢሲ በላከው መግለጫ፤ የአዲስ አበባ ከተማን ሰላምና ደኅንነት የበለጠ በማጠናከር በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ እጀባና አስተማማኝ ጥበቃ በማድረግ ጉባኤዎቹ በሰላም እንዲጠናቀቁ ማስቻሉን ገልጿል። መላው የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አመራርና አባላት የተሰጣቸውን…


