የተፈጥሮ ኃብትን በኃላፊነት የማልማት አይነተኛ ማሳያ የቱሉ ካፒ የወርቅ ፕሮጀክት ነው፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምዕራብ ወለጋ ዞን ገንጂ ወረዳ የሚገኘውን የቱሉ ካፒ የወርቅ ልማት ፕሮጀክትን ጉኝተዋል። በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፣ ፕሮጀክቱ የተፈጥሮ ኃብታችንን ለሀገርና ለሕዝብ ጥቅም በኃላፊነት እንዴት ማዋል እንደምንችል የሚያሳይ አይነተኛ ምሳሌ መሆኑን ገልጸዋል። በመንግሥት እና በግል ኢንቨስተሮች ትብብር እየተከናወነ የሚገኘው ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት፣ ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው ባሻገር የአካባቢውን ማኅበረሰብ የኑሮ ደረጃ የሚያሻሽሉ በርካታ…


