ለሕዝባችን መከታ፤ ለኢትዮጵያ ጠላቶች ደግሞ መቅሰፍት ነን – ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ
የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እና ለመንግሥት መከታ፣ ለጠላቶቿ ደግሞ መቅሰፍት ነው ሲሉ የዕዙ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ ገለጹ። በሐዋሳ ከተማ እየተከበረ በሚገኘው የዕዙ 65ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ላይ ንግግር ያደረጉት ዋና አዛዡ፣ የኢትዮጵያ ጠላቶች ከጥፋት ድርጊታቸው የማይታቀቡ ከሆነ የሠራዊቱ ክንድ ብርቱ መሆኑን አስጠንቅቀዋል። ጀግንነት የኢትዮጵያ ቀደምት የታሪክ አሻራ መሆኑን የጠቀሱት ሌተናል ጄኔራል…


