እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!

አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ ዒድ አል ፈጥር በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ልዩ ትርጉም ያለው የቅዱሱ የረመዳን የፆም ወር ማሳረጊያ ታላቅ በዓል ነው፡፡ ዕለቱ ሕዝበ ሙስሊሙ በቅዱሱና በታላቁ የረመዷን ወር ለሀገራችን ሰላምና ፀጋ፤ ለመላው ህዝባችን ፍቅርና አንድነት ወሩን ሙሉ በፆምና በዱአ አሳልፎ ከፈጣሪ እዝነትና በረከት የሚቀበልበት ልዩ ቀን ነው፡፡ የዒድ…

Read More

እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሰን!አደረሳች

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የንግድ ኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀርቢ ቡህ እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል ዒድ አል ፈጥር በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ልዩ ትርጉም ያለው የቅዱሱ የረመዳን የፆም ወር ማሳረጊያ ታላቅ በዓል ነው፡፡ በዓሉ ሕዝበ ሙስሊሙ በረመዳን ወቅት ሲያደርገው እንደነበረው በአንድነት ተሰባስቦ ያለው ለሌለው በማካፈል ማህበራዊ ትስስሩን ይበልጥ…

Read More

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር 1447ኛው የኢድ አልፈጥር በአል አስመልክቶ ያስተላለፉት መልዕክት

እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል-ፊጥር ረመዳን በዓል፥ በሰላም እና በጤና አደረሰን/አደረሳችሁ። ያሳለፍነው የረመዳን ጾም ወር ፥ ዋነኛ ሥርዓቶች ከሆኑት የፀሎት እና የስግደት መንፈሳዊ ተግባራት በተጨማሪ ፥ በብዙ የበረከት ሥራዎች የታጀበ ወር ነበር። ዘንድሮ የረመዳን ወር እና የክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዐቢይ ጾም በተመሳሳይ ቀን በመጀመራቸው ፥ ከጥንትም ‘በትንሿ ኢትዮጵያ’ #ድሬዳዋ ህብረተሰብ ውስጥ የኖረው የፍቅር እና አብሮነት ውብ…

Read More

የመደመር አንቀጽ

የማይበገር ኢኮኖሚ መገንባት ብዙ ዓምዶች አሉት። አደጋን አስቀድሞ አይቶ ማስወገድ ወይም መከላከል አንዱ ነው። አደጋው ከመጣም አደጋውን ተቋቁሞ ማሳለፍ ሌላው ነው። አደጋው ጉዳት ካደረሰም በቶሎ ለማገገም የሚችል ኢኮኖሚን መገንባት ደግሞ ሌላው የማይበገር ኢኮኖሚ ጠባይ ነው። የመደመር መንግሥት ኢኮኖሚውን የሚፈትኑ አደጋዎችን ማስጠም የሚችል ነው። ተለዋዋጭ ነገሮችን ይላመዳል፤ እንዲሁም ከአደጋ ቶሎ የሚያገግም ኢኮኖሚ መገንባት ትልቁ ትኩረቱና መገለጫው…

Read More

የውሀ አምራች ፋብሪካዎች ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በማድረጋቸው አስተዳደራዊ እርምጃ ተወሰደ::

በአስተዳደሩ የውሀ አምራች ፋብሪካዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በራሳቸው ተነሳሽነት ባደረጉት የዋጋ ጭማሪ ተጠቃሚውን ማህበረሰብ ይቅርታ ጠይቀዋል። ከአስተዳደሩ ንግድ እንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ጋር ውይይት ያደረጉት የውሀ አምራች ፋብሪካ ባለቤቶች እና ስራ አስኪያጆች እንደተናገሩት አለማቀፋዊ የገበያ ሁኔታ ተከትሎ የጥሬ እቃው መጨመር ጋር ተያይዞ ከሁለት ወራት በላይ ዋጋ ቢጨምርም ዋጋ ሳይጨምሩ መቆየታቸውን እና አሁናዊ የጥሬ እቃ ዋጋ ጭማሬ…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከእስራኤል ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ ጋር ተወያዩ::

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ለይፋዊ ጉብኝት የመጡትን የእስራኤል ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግን ተቀብለው ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ እና እስራኤልን ግንኙነት በማጤን በወል ፍላጎታችን ላይ ተመሥርተን ትብብራችንን የምናሳድግባቸውን መንገዶች ተመልክተናል ሲሉም አክለዋል።

Read More

ውጊያን የሚያስቀር አየር ወለድ፦ የኢትዮጵያ አዲሱ የጥንካሬ መገለጫ::

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በልዩ ዘመቻዎች ዕዝ 65ኛው የምስረታ በዓል ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የሀገሪቱ የመከላከያ አቅም ወደ አዲስ ምዕራፍ መሸጋገሩን አብስረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ወቅት እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ አሁን ላይ የገነባችው ልዩ ኃይል ተራ ተዋጊ ብቻ ሳይሆን፣ ውጊያን የሚያስቀር እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም ውጊያን በአጭር የሚቀጭ ብቃት ያለው ነው። እነዚህ ባለሁለት…

Read More

የገጸ ምድር እና የከርሰ ምድር የውኃ ሃብቶችን ለመስኖ ልማት የማዋል ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በግብርናው ዘርፍ መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት እየተከናወኑ ካሉ ሥራዎች መካከል የሀገራችንን የገጸ ምድርና የከርሰ ምድር የውኃ ሃብቶች ለመስኖ ልማት የማዋሉ ተግባር ዋነኛው ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ከዚህ ቀደም ምንም ዓይነት ጥቅም ሳይሰጡ የቆዩ በርካታ አካባቢዎች በአሁኑ ወቅት በመስኖ ልማት አማካኝነት ወደ ግብርና ማዕከልነት እየተቀየሩ መሆኑን ነው ያስታወቁት። ለዚህም የብላቴ ወንዝ የሚገኝበት አካባቢ…

Read More

“ሠራዊታችን በድሮን የመሰለል እና በካሚካዚ ምሽግን የማፈራረስ አቅም ያለው ነው” – የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በድሮን የመሰለል እና በካሚካዚ ምሽግን የማፈራረስ አቅም ያለው ነው ሲሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ይህ ኃይል ከሱማሌ ጫፍ እስከ ምጽዋ ጫፍ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የሽብር ጥቃቶችን የመከላከል እና የቀጠናውን ደኅንነት የማስጠበቅ ብቃት እንዳለውም አረጋግጠዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሐዋሳ በተካሄደው የ65ኛው የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ የምሥረታ በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር፣…

Read More