የገጸ ምድር እና የከርሰ ምድር የውኃ ሃብቶችን ለመስኖ ልማት የማዋል ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በግብርናው ዘርፍ መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት እየተከናወኑ ካሉ ሥራዎች መካከል የሀገራችንን የገጸ ምድርና የከርሰ ምድር የውኃ ሃብቶች ለመስኖ ልማት የማዋሉ ተግባር ዋነኛው ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ከዚህ ቀደም ምንም ዓይነት ጥቅም ሳይሰጡ የቆዩ በርካታ አካባቢዎች በአሁኑ ወቅት በመስኖ ልማት አማካኝነት ወደ ግብርና ማዕከልነት እየተቀየሩ መሆኑን ነው ያስታወቁት።

ለዚህም የብላቴ ወንዝ የሚገኝበት አካባቢ እንደ ዋነኛ አብነት ተጠቃሽ መሆኑን ጠቁመው፣ በአካባቢው የግል ባለሃብቶችን በማሳተፍ ሰፋፊ የፍራፍሬ ልማቶች እየተከናወኑ እንደሚገኙ አመላክተዋል።

እነዚህ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ለምታደርገው ጥረት ከፍተኛ እገዛ እንደሚያበረክቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመልዕክታቸው ገልጸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *