የፖለቲካ ፓርቲዎች ሃሳቦቻቸውን ለህዝብ ተደራሽ የሚያደርጉበት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል
በምርጫው የሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሃሳቦቻቸውን ለህዝብ ተደራሽ የሚያደርጉበት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን የድሬዳዋ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት አስታወቀ። ፓርቲዎች የፖሊሲ ሀሳቦቻቸውን ለህዝብ ተደራሽ በማድረግ ምርጫው ዴሞክራሲያዊ፣ አሳታፊና ሰላማዊ እንዲሆን የድርሻውን እየተወጣ መሆኑንም ገልጿል። የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጣሂር ሮብሌ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ዘንድሮ በሚካሄደው 7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚሳተፉ የፖለተካ ፓርቲዎች የድርጅቱን የቴሌቪዥን እና የሬድዮ ጣቢያዎች ተጠቅመው አማራጭ…


