ለድሬዳዋ አስተዳደር ነዋሪዎች በሙሉ!

በመካከለኛው ምስራቅ ቀጣና የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ ይገኛል፡፡

ይህን ተክሎም ሀገራት በቀጣናው በተፈጠረው ቀውስ ሳቢያ የተከሰተውን የነዳጅ እጥረት ለመቋቋም የተለያዩ ርምጃዎችን መውሰድ ጀምረዋል፡፡

በዓለም ግዙፍ ኢኮኖሚ ያላቸው ቻይና እና ጃፓን ጨምሮ ሌሎች ሀገራት አይቀሬ የሚመስለውን የነዳጅ እጥረት ለመቋቋም የተለያዩ ውሳኔዎችን እያሳለፉ ይገኛሉ፡፡

በመካከለኛው ምሥራቅ በተፈጠረው ቀውስ ምክንያት፣ ሀገራችንን ጨምሮ ነዳጅ ገዝተው የሚጠቀሙ ሀገራት አቅርቦቱን እንደልብ ለማግኘት ተቸግረዋል።

በመሆኑም፣ ችግሩ ተፈትቶ ወደ መደበኛው የነዳጅ አቅርቦት ሥርዓት እስክንመለስ ድረስ ነዳጅን በቁጠባ መጠቀም ይኖርብናል።

ስለሆነም የአስተዳደሩ ነዋሪዎች አጫጭር መንገዶችን በእግር በመጓዝ፣ እንዲሁም የብስክሌት አማራጮችን በመጠቀም እንድትተባበሩ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

አቶ ከድር ጆሀር

የአስተዳደሩ ክቡር ከንቲባ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *