በአስተዳደሩ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተገለፀ::

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የድሬዳዋ አስተዳደር ጉብኝት ተከትሎ በተሰጡ አቅጣጫዎችና በቀጣይ ስራዎች በየደረጃው ያሉ አመራሮች ጋር ውይይት ተካሂዷል ።

በውይይቱም የኢ.ፌ.ድ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በድሬዳዋ አስተዳደር ጉብኝት ካደረጉ በኋላ የሰጡትን አቅጣጫ ተከትሎ በአተገባበሩ ዙሪያ በተካሄደው የምክክር መድረክ ላይ የስራ እቅድ ያቀረቡት በብልዕግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ላይም ማብራሪያ ሰጥተዋል ።

በውይይቱም የኢንዱስትሪ ልማትን በተመለከተ የተገልጋይን ቅሬታ መፍታትና አገልግሎትን ማቀላጠፍ ፣ ዘመናዊ ግብርናና የመስኖ ልማት፣ የኮሪደር ልማት ፣ ከተማ ማደስ ፣ የቱሪዝም ልማት፣ የአስተዳደሩን ገቢ ማሳደግ እንደሚገባም አቶ ኢብራሂም በእለቱ አንስተዋል።

ከዚህ ባለፈም የኢኮኖሚ ልማትን በማሳደግ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ በሚቻልበት ረገድ ኢንቨስትመንትን በመሳብ የኮንስትራክሽን አቅርቦት ላይ ባለሃብቱ እንዲሰማራ መንገዶች ምቹ ማድረግ እንዳለባቸውም ተናግረው እየጨመረ የመጣውን የህዝብ ቁጥር መሠረት ያደረገ በተለይ ወጣቱን የስራ ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል ።

በድሬዳዋ አስተዳደር የተጀመሩ የልማት ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ሃርቢ ቡህ ተናግረው ከሌማት ትሩፋት ጋር ተያይዞ በርካታ ስራዎችን መስራት እንደሚገባና በአስተዳደሩ ላይ ያሉ ፋብሪካዎችም ምርቶቻቸውን ለነጋዴው በቀጥታ እንዲደርሳቸው ከማድረጉ ጋር ተያይዞ በቀጣይ በትኩረት መስራት እንደሚገባም ነው አቶ ሀርቢ ቡህ በውይይት መድረኩ ላይ ያስታወቁት ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *