ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አልፈጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የአስተዳደሩን ህዝብ የልማትና የዲሞክራሲ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ አስተዳደራዊ አዋጆችንና ደንቦችን በማውጣትና በምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች የአዋጆችንና ደንቦችን በፈጻሚው የመንግስት አካል ተፈጻሚነታቸውን በመከታተል እና በአፈጻጸማቸው መሰረት አስፈላጊ ውሳኔዎችን በመስጠት ምክር ቤቱ ከህዝብ የተጣለበትን ሃላፊነት በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡
በመሆኑም የምክር ቤቱ ከፍተኛ የስልጣን ባለቤት በሆነው ህዝብ ይሁንታ የተመረጠ የህዝብ ተወካይ እንደመሆኑ መጠን በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫም ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የአስተዳደራችንን የዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ግንባታ ማስቀጠል ይገባናል ፡፡
የኢድ አልፈጥር በአልን ስናከብርም በታላቁ የረመዳን ወር የእስልምና አስተምህሮ በሚያዘው ሀይማኖታዊ ትእዛዝ መሰረት ስናደርግ እንደነበረው አቅመ ደካሞችን እና ችግረኞችን በመርዳት በአሉን በደስታ እንዲያከብሩ እንድናደርግ ጥሪዬን እያስተላለፍኩ መልካም የኢድ አልፈጥር በአል እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ፡፡
የተከበሩ አብዲ ሙክታር
የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት አፈ ጉባኤ


